ስለቴ
Silete
2010 · ትራክ 1 · 3:02 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ ጩሀቴን ሰምተሃል ምሬቴን የልመናዬን ቃል
በራሴ ያለቀስኩበት ቀን በጊዜው ቀን ተብቆ ሰርቷል
ውዲዬ ስምህን ላነሳሳው ሺ ጊዜ እልፍም ላወድሰው
አባትዬ አላፈርኩብህም አምኜ አልፌብሃለው ተግባርህ ቃልህ ነው
አዝማች · Chorus
ስለቴ ሰመረ ስለቴ ሰመረ
ከሰው ግምት ያንተ በለጠ ከጠበኩህ የበለጠ
ከእኔው ግምት ያንተ በለጠ ከጠበኩህ የበለጠ
ቁጥር 2 · Verse 2
ገረመኝ ለኔስ ደነቀኝ አሄ
ቁጥር 3 · Verse 3
ዉለታህ በዝቶብኝ እንዲህ ይስደነከኝ
ምን አይተህብኝ ነው ለዚህ ያበቃሀኝ
ዉለታህ በዝቶብኝ እንዲህ ካስደነከኝ
ምን መልሳለው ዉዴ ክበር ያከበርከኝ
አቤቱ ዉስቴን አድምጠሃል ጭንቀቴም ስጋቴም ገብቶሃል
ውድቀቴን ያለምኩበት ለሊት የደስተ የድል ሆኖልኛል
ውዲዬ ምስጋና አይነስህ ትምክቴም አቅሜም ልበልህ
ደራሽዬ እኔ አይቼሃለው ሳትዘገይ ኤልፌብሃለው ተግባርህ ቃልህ ነው
አዝማች · Chorus
ስለቴ ሰመረ ስለቴ ሰመረ
ከሰው ግምት ያንተ በለጠ ከጠበኩህ የበለጠ
ከእኔው ግምት ያንተ በለጠ ከጠበኩህ የበለጠ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ