ምሳሌዬ
Mesalieyie
2010 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምሳሌዬ አንተው ነህ በምግባርህ የማውቅህ
ንግግርህ ከሩቅ ይጠራል ጨዋነትን ተላብሰሃል
ከውስጤ ገብተህ ቀርተሃል ማን ቢፈለግ ይተካሃል
ጥበብ ፍቅርም በአንተ ይለካል አዋቂነትስ ከአንተ ይቀዳል
አዝማች · Chorus
አስተዋይ ወዳጄ ብልህ ብትገባኝ ነው ባውቅህ
ጠቢብ ብዬ ብጠራህ ቃል አጥቼ ለስምህ
ጻድቅ ፍፁም ነህ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አለቅነት በአንተ ያምራል አስተዳደር በአንተ ይሰላል
መታገስህ ሁሉን ያልፋል መቼ ፍርድህ ቀድሞ ያውቃል
የሊቅ ጥጉ መደምደሚያ የትሁት ልብ ማሳረጊያ
ፍትህ ሚዛኑ በአንተ ከወጣ ዳኝነቱም ካንተ ይምጣ
አዝማች · Chorus
አስተዋይ ወዳጄ ብልህ ብትገባኝ ነው ባውቅህ
ጠቢብ ብዬ ብጠራህ ቃል አጥቼ ለስምህ
ጻድቅ ፍፁም ነህ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሁሉን ከፍታ ይዘሃል ወርደህም አዳምን ሁነኃል
ከፍም ብለህ ዝቅም ብለህ ፍፁም ጌታ አንድ አንተ ነህ
ሁሉን በእኩል የምታየው ምስኪኑንም የማትንቀው
የደግነት መገለጫ የሁሉ አባት አንተ ብቻ
ውዴ ውበትህ ማንነትህ ደም ግባትህን
አይቼው አይቼው አልችልም ልገልጽህ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ