በደሌን ሽረሃል
Bedelen Shirehal
2010 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስፍራን አዘጋጅተህ እኔን ከጠራኀኝ
በክብር እንድኖር ወደኅኝ ከአዳንከኝ
ከእስትንፋሴ ይልቅ ቀርበኀኛልና
ውዴ ተቀበለኝ የልቤን ምሥጋና
አዝማች · Chorus
በዋጋ ገዝተኀኛል ከእንግዲህ ምን ያሰጋኛል
የዚች ምድር አይደለሁምና
በስምህ ላብዛልህ ምሥጋና
በደሌን ሽረሃል እኔን ግን ወደሃል
ሞቴን ወስደህ ከእኔ ሞትክልኝ መድህኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የዳነን ማንነት ከአንተ አግኝቻለሁ
ሥጋቴን ጭንቀቴን ለአንተው ትቼዋለሁ
ፍፁም ሰላም በአንተ ከአንተ ሆኖልኛል
ለዘለዓለም መኖር መብቱ ተሰጥቶኛል
አዝማች · Chorus
በዋጋ ገዝተኀኛል ከእንግዲህ ምን ያሰጋኛል
የዚች ምድር አይደለሁምና
በስምህ ላብዛልህ ምሥጋና
በደሌን ሽረሃል እኔን ግን ወደሃል
ሞቴን ወስደህ ከእኔ ሞትክልኝ መድህኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የፈሰሰልኝ ደም በእውነት ደምህ ነው
ሕይወት የሆነልኝ ሙት ለነበርኩት ሰው
እንዳልጠፋ አድርገህ አንተ አድነኀኛል
ላደረክልኝ ሁሉ መልሴ ያንስብሃል
አዝማች · Chorus
በዋጋ ገዝተኀኛል ከእንግዲህ ምን ያሰጋኛል
የዚች ምድር አይደለሁምና
በስምህ ላብዛልህ ምሥጋና
በደሌን ሽረሃል እኔን ግን ወደሃል
ሞቴን ወስደህ ከእኔ ሞትክልኝ መድህኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ