ጌታዬ እኮ ነው
Gietayie Eko New
2007 · ትራክ 6 · 7:04 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታዬ እኮ ነው ሰው ያረገኝ
ከወደቅኩበት ያነሳኝ (፪x)
ያነሳኝ ያነሳኝ ያነሳኝ
አዝማች · Chorus
ቆም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፊት ያቆመኝ ጌታዬ እኮ ነው (፫x)
ጌታዬ አንተ የእኔ እረኛ
ኢየሱስ አንተ የእኔ እረኛ
የእኔ እረኛ ነህ የእኔ እረኛ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ ነህ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ
ከክፉ ያዳንኸኝ የጋረድከኝ ኢየሱስ
ለዛሬም አልፈራም አንተን ታምኛለሁ
ለነገም አልፈራም እኔ አንተን ይዤአለው (፪x)
አዝማች · Chorus
ቆም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፊት ያቆመኝ ጌታዬ እኮ ነው (፫x)
ጌታዬ አንተ የእኔ እረኛ
ኢየሱስ አንተ የእኔ እረኛ
የእኔ እረኛ ነህ የእኔ እረኛ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተ ነህ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ
ከክፉ ያዳንኸኝ የጋረድከኝ ኢየሱስ
የሚጠብቀኝን የሞት ፅዋ ደፍተህ
እንዳይብረከረክ ጉልበቴን አፅንተህ
ዓለት ላይ እንደ ቆመው እንዳማረው ቤትህ
ሕይወቴ ተዋበ አንተ የገባህ ለት
አዝማች · Chorus
ቆም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፊት ያቆመኝ ጌታዬ እኮ ነው (፫x)
ጌታዬ አንተ የእኔ እረኛ
ኢየሱስ አንተ የእኔ እረኛ
የእኔ እረኛ ነህ የእኔ እረኛ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ ነህ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ
ከክፉ ያዳንኸኝ የጋረድከኝ ኢየሱስ
አጋር ሆነኸኛል ከፉ እንዳይነካኝ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠነከክልኝ
የጸና ግንብ ነው ሥሙ ያስጠልላል
አንተን የታመነ መች ክፉ ያገኘዋል
ጌታዬ እኮ ነው ሰው ያረገኝ
ከወደቅኩበት ያነሳኝ (፪x)
ያነሳኝ ያነሳኝ ያነሳኝ
አዝማች · Chorus
ቆም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፊት ያቆመኝ ጌታዬ እኮ ነው (፫x)
ጌታዬ አንተ የእኔ እረኛ
ኢየሱስ አንተ የእኔ እረኛ
የእኔ እረኛ ነህ የእኔ እረኛ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ