አልመዝንህም
Almezenehem
2007 · ትራክ 7 · 5:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ይህንን ጌታ ነው ጌታዬ ነህ ያልኩት
ጨለማውን አይቶ ልቡ የማይደነግጥ (፪x)
የችሎቱ ብዛት እጅግ ይገርመኛል
ውኃውን እረግጠህ ና እንጂ ና ልጄ አትፍራ ይለኛል (፪x)
አትፍራ ይለኛል
አዝማች · Chorus
እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም
እስከመጨረሻው አትችልም አልልም
ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል
ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል
ለየት እኮ ይላል ለየት
ለየት እኮ ይላል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አልመዝንህም ስለሆነና ስላልሆነ
እምነቴ ዛሬም ትኩስ ነው መች ቀዘቀዘ
አያሳልፍም እኔስ አልልም ውኃውን አይቼ
ቀጥ ያለ መንገድ ይሆናል ስላለ ጐኔ
አዝማች · Chorus
እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም
እስከመጨረሻው አትችልም አልልም
ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል
ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል
ለየት እኮ ይላል ለየት
ለየት እኮ ይላል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በእኔ ውስጥ ያለው ይሄ ኢየሱስ መቼ ደክሞ ያውቃል
ግራ አይገባው እንደ ሰው የት ይሸበራል
ብቻ ከፊቴ ችግር ሲጋረጥ እንዲህ ይለኛል
መፍትሄ የአንተ ነው ተሻገር እንጂ እረፍ ይለኛል
አዝማች · Chorus
እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም
እስከመጨረሻው አትችልም አልልም
ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል
ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል
ለየት እኮ ይላል ለየት
ለየት እኮ ይላል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ደመናን አይቶ ትንቢት መናገር ሁሉም ይችላል
ንፋሱ ሲነፍስ ሰው ሁሉ ይዘንባል ይላል
የእኛ ጌታ ግን ለየት ያለው ነው ትንቢት ሲናገር
ውኃን ያመጣል እንዲሁ ደመና ሳይኖር
አዝማች · Chorus
እስከሚሆን ድረስ ብቻ አላምንህም
እስከመጨረሻው አትችልም አልልም
ውኃውን እረግጠህ ማን ጀግና ና ይላል
ከብዙ አማልክት የእኔ ጌታ ለየት እኮ ይላል
ለየት እኮ ይላል ለየት
ለየት እኮ ይላል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ