አልገፋ ያለውን ቀን
Alegefa Yalewen Qen
2007 · ትራክ 5 · 7:56 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አልገፋ ያልውን ቀን
ክንድህ ገፍቶት አሻገርከኝ
ሁሉን ችዬ በአንተ አለፍኩ
መቸገሬን አስረሳኸኝ
ማን ልበልህ ምን ልበልህ
ምላሽ አጣሁ ጌትዬ የምከፍልህ አዎ
ዝቅ ብዬ ክብሬን ጥዬ
ልስገድልህ ጌታዬ ተዋርጄ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከኋላዬ ርቆ እንደ ህልም አለፈ
እንደ ፈሳሽ ውኃ መጨነቄ ሄደ (፪x)
ምሥጋናዬ አርጐ መቅደስህን ይሙላው
ለውለታህ ምላሽ ይሄም ሲያንስብህ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
አልገፋ ያልውን ቀን
ክንድህ ገፍቶት አሻገርከኝ
ሁሉን ችዬ በአንተ አለፍኩ
መቸገሬን አስረሳኸኝ
ማን ልበልህ ምን ልበልህ
ምላሽ አጣሁ ጌትዬ የምከፍልህ አዎ
ዝቅ ብዬ ክብሬን ጥዬ
ልስገድልህ ጌታዬ ተዋርጄ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እጅህ እየረዳኝ ሁሉን ተሻገርኩ
አልገፋ ያለውን ቀኖቼን አለፍኩ (፪x)
ለአደረከው ሥራ ምሥጋና ይገባሃል
ነፍስ ያለው ግዑዙ ወድቆ ይሰግድልሃል (፪x)
አዝማች · Chorus
አልገፋ ያልውን ቀን
ክንድህ ገፍቶት አሻገርከኝ
ሁሉን ችዬ በአንተ አለፍኩ
መቸገሬን አስረሳኸኝ
ማን ልበልህ ምን ልበልህ
ምላሽ አጣሁ ጌትዬ የምከፍልህ አዎ
ዝቅ ብዬ ክብሬን ጥዬ
ልስገድልህ ጌታዬ ተዋርጄ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምን ቢሰጥህ ምላሽ የአንተን ሥራ ይተካል
እንዲያው ዝቅ ብሎ ማመስገን ይሻላል (፪x)
እስከ ምድር ዳርቻ የሚመስልህ ታጥቷል
ትልቁ እግዚአብሔር ክብር ይገባሃል (፪x)
የእኔ ኢየሱስ የእኔ አባት የእኔ ጌታ
አንተ ነህ የእኔ ባለ ውለታ (፪x)
ላብዛልህ አምልኮ ላብዛልህ
ላብዛልህ ስግደትም ላብዛልህ (፪x)
የእኔ ኢየሱስ የእኔ አባት የእኔ ጌታ
አንተ ነህ የእኔ ባለ ውለታ (፪x)
ላብዛልህ አምልኮ ላብዛልህ
ላብዛልህ ስግደትም ላብዛልህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ