Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምላክ ያለው ይምጣ

Amlak Yalew Yemta

2007 · ትራክ 4 · 4:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላክ ያለው ይምጣ የእኔ አምላክ ልዩ ነው

በምድረ በዳ ላይ ማኖር ልማዱ ነው (፪x)

እስቲ ልፎካከር በሰሜን በደቡብ

በምስራቅ በምዕራብ እርሱ ነው እግዚአብሔር (፪x)

ትልቅ ነው ብዬ መታሁት እንጂ መቼ ፈራሁት

በበረሃ ውስጥ አስተምሮኛል ኑሮ የእኔ አባት (፪x)

የተደበቀው ፀጋ ሲወጣ ከኮሮጆዬ

መውደቁን አውቆ ፈርቶ ሸሽቶኛል ባለ ጋራዬ (፪x)

አምላክ ያለው ይምጣ የእኔ አምላክ ልዩ ነው

በምድረ በዳ ላይ ማኖር ልማዱ ነው (፪x)

እስቲ ልፎካከር በሰሜን በደቡብ

በምስራቅ በምዕራብ እርሱ ነው እግዚአብሔር (፪x)

የተዘጋው ከፈተውና ከፊት ከፊቴ

መሸነፍ ሳይሆን ያጋጥመኛል ድል በሕይወቴ (፪x)

የተዘራውን በቅሎ አየሁት አልጨነገፈም

በድርቁ ወራት የሌላው ሲደርቅ የእኔ አልደረቀም (፪x)

አምላክ ያለው ይምጣ የእኔ አምላክ ልዩ ነው

በምድረ በዳ ላይ ማኖር ልማዱ ነው (፪x)

እስቲ ልፎካከር በሰሜን በደቡብ

በምስራቅ በምዕራብ እርሱ ነው እግዚአብሔር (፪x)

ምን ልበል ምን ላድርግ ልቤ መደነቅ ተሞላ

በአንዱ ስገረም ሌላው እዚህ ደግሞ

ተዓምር ነው ከማለት ሌላ

ድንቅ ነው ከማለት ሌላ

ልዩ ነው ከማለት ሌላ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ