ደግሞ ቀኑ ሲጨልም
Degmo Qenu Sichelm
2007 · ትራክ 2 · 5:13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠዋት ስነሳ ደስታ ይሆናል
የትላንትናው ሃዘን ይርቃል
እህል ባልበላም ፊትህ ያጠግበኛል
ፀጋህ ከክፉ ይጋርደኛል
ምህረትህ ከፊት ከኋላ ከቦኝ
አቤት ይገርማል ስንቱን አለፍኩት
አዝማች · Chorus
ደግሞ ቀኑ ሲጨልም
ደግሞ ቀኑ ሲነጋ
ደግሞ እርጥቡ ሲደርቅ
ደግሞ ሁኔታ ሲርቅ
አንዴ ወዶኛል (፬x) ምን ያሰጋኛል
አንዴ ወዶኛል (፬x) ምን ያሰጋኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
አምላክ ሲረዳኝ አታዩም ዎይ
ክረምቱ አልፎ በጋው ሲታይ
ከዓለቱ ልውጣ ድምጼን ላሰማ
ጌታ እንደ ረዳኝ ሰው ሁሉ ይስማ
ያገለገልኩት ለሥሙ የለየኝ
ቀን ቆጠረና ዋጋ ከፈለኝ
አዝማች · Chorus
ደግሞ ቀኑ ሲጨልም
ደግሞ ቀኑ ሲነጋ
ደግሞ እርጥቡ ሲደርቅ
ደግሞ ሁኔታ ሲርቅ
አንዴ ወዶኛል (፬x) ምን ያሰጋኛል
አንዴ ወዶኛል (፬x) ምን ያሰጋኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ