የሕይወቴ እረኛ
Yehiwotie Eregna
2007 · ትራክ 11 · 4:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኮ አንተ የሕይወቴ መሪ ነህ
አንተ የሕይወቴ እረኛ ነህ
ልቤን ለአንተ ትቼዋለሁ
ዘለዓለም አምልክሃለሁ (፫x)
እውነትን ልናገር አይዋሽ አንደበቴ
ውስጤን ያሳረፈው ኢየሱስ ነው አባቴ
ሁሉንም አስናቀኝ እኔም ሁሉን ተውኩት
ጌታዬ እንደሚሻል ውስጤን አሳመንኩት
አዝማች · Chorus
አለኝ ልበል
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔ አለኝ ልበል
አለኝ ልበል አባት
ውስጤ ያረፈበት/የኮራበት (፪x)
ከሲና መጣ የእግዚአብሔር ክብር
ሕግን ሊያወጣ ለዚች ለምድር
በእራሱ ፈቃድ የሚጓዘውን ሕዝብ
በእግዚአብሔር ፀጋ እንዲተዳደር
ካለፈው ኪዳን የሚሻል ኪዳን
የእግዚአብሔር ክብር ኢየሱስ መጣ
በሰው ጫንቃ ላይ የተቀመጠው ቀንበር ተፈታ
አዝማች · Chorus
አለኝ ልበል
ቁጥር 3 · Verse 3
እኮ አለኝ ልበል
አለኝ ልበል አባት
ውስጤ ያረፈበት (፪x)
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው
የሚያሳጣኝም የለም
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል
በእረፍቱ ውኃ ዘንድ ይመራኛል
ነፍሴን መለሳት
ስለ ሥሙም በፀድቅ መንገድ መራኝ [1]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ