የግሌ ነህ
Yegelie Neh
2007 · ትራክ 10 · 5:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘማሪ አውታሩ ከበደ
ርዕስ አብ ያከበረው
አልበም ተነስቷል
በጓዳዬ ሆኜ ቅዱስ ነው ስለው
በአደባባይ ላይ ሥራዬን ሰራው
ልቤ ቅልጥ አለ በፍቅሩ ትኩሳት
ሰላም ነው የሞላው ብትገቡ በእኔ ቤት
አዝማች · Chorus
አሃሃ ከምድር በታች ከዚያም በላይ
እኔ አላየሁም እርሱን መሳይ (፪x)
አብ ያከበረ ጌታ እርሱን ብቻ
ለውበቱማ የለውም አቻ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዝምታ ሆነ ፀጥታ
አካባቢው ላይ ምን መጣ
ምትሃት አይደለም ጌታ ነው
ማዕበል ወጀቡን ያቆመው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ነው (፪x) ከሁሉ በላይ
ከሁሉ በላይ
በሰማይ በምድር የለም የሚታይ
የለም የሚታይ
እስቲ ከእርሱ በላይ ማነው የበላይ
ማኅተሙን የፈታ ይታወቃል ዎይ
እስቲ ከእርሱ በላይ ማነው የበላይ
ሞትን ድል የነሳ ይታወቃል ዎይ
አዝማች · Chorus
አሃሃ ከምድር በታች ከዚያም በላይ
እኔ አላየሁም እርሱን መሳይ (፪x)
አብ ያከበረ ጌታ እርሱን ብቻ
ለውበቱማ የለውም አቻ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ