ክብርህን ላየ
Kibrehen Laye
2020 · ትራክ 8 · 5:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብርህን ላየ ለተረዳ ሰው
አንተን ማምለክ እጅግ ቀላል ነው
ዝም ብዬ አመልክሃለሁ
የኔን ጉዳይ አንተው አንተው አንተው ጨርሰው
አዝኜ ልቤ ተሰብሮ
ሳላውቅህ ሳላውቅህ ድሮ
ብጣራም (2)
ብጮህም (2)
አዝማች · Chorus
የሚሰማኝ አላገኘሁም
ግን ኢየሱስ ደረሰልኝ
ከላይ ሆኖ ልጁን ላከልኝ
ወድቄ ሳለው ከጨለማው
እርሱ ብቻ ነው እኔን ያየው
ስላየኸኝ ደስ ብሎኛል ስላየኸኝ
በባዶ ሜዳ ዝም ብለህ ስላልተውከኝ
ስላሰብከኝ ደስ ብሎኛል ስላሰብከኝ
በምድረበዳ ዝም ብለህ ስላልተውከኝ
ተመስገንልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
አዝኜ ልቤ ተሰብሮ
ሳላውቅህ ሳላውቅህ ድሮ
ብጣራም (2)
ብጮህም (2)
የሚሰማኝ አላገኘሁም
ግን ኢየሱስ ደረሰልኝ
ከላይ ሆኖ ልጁን ላከልኝ
ወድቄ ሳለው ከጨለማው
እርሱ ብቻ ነው እኔን ያየው
ቁጥር 3 · Verse 3
አለፈ ያ ዘመን
አለፈ ያ ጊዜ
አለፈ ያ ለሊት
አለፈ ያ ጊዜ
ስላለፈ ደስ ብሎኛል ስላለፈልኝ
በባዶ ሜዳ ዝም ብለህ ስላልተውከኝ
ስላለፈ ደስ ብሎኛል ስላለፈልኝ
በምድረበዳ ዝም ብለህ ስላልተውከኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ክብርህን ላየ ለተረዳ ሰው
አንተን ማምለክ እጅግ ቀላል ነው
ዝም ብዬ አመልክሃለሁ
የኔን ጉዳይ አንተው አንተው አንተው ጨርሰው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ