Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰማ ሰማ

Sema Sema

2020 · ትራክ 5 · 5:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰማ ሰማ ጸሎቴን ሰማ

አየ አየ መገፋቴን

ፍረድ ብዬ የጮኽኩትን

ፍረድልኝ ብዬ ያልኩትን (፪x)

አቤት አፈረ አፈረ ጠላቴ

አቤት ከሰረ ከሰረ ጠላቴ

እዬዬ ነው በጠላት መንደር

በህይወቴ ላይ እግዚአብሔር ሲከብር

ሰማ ሰማ ጸሎቴን ሰማ

አየ አየ መገፋቴን

ፍረድ ብዬ የጮኽኩትን

ፍረድልኝ ብዬ ያልኩትን (፪x)

ስማማ ስማ ጠላቴ

ቁርጡን ቁርጡን እወቀው

እኔ እንደው ማምለኬን አልተው / እኔ መዘመሬን/ማገልገሌን አልተው

ያለቀለት ነገር ነው

መስሎት ነበር ያበቃልኝ

መስሎት ነበር ያለቀልኝ

አይ ሞኜ አይ ሞኜ አላወቀኝ

እግዚአብሔርን እንደያዝኩኝ

አይ ሞኜ አይ ሞኜ መቼ አወቀኝ

እግዚአብሔርን እንደያዝኩኝ

አንተን ብሎ ማን አፈረ

ማ ከሰረ ማ ከሰረ

አንተን ብሎ ማ ዘገየ

ከሰው ሁሉ የተለየ

ሰማ ሰማ ጸሎቴን ሰማ

አየ አየ መገፋቴን

ፍረድ ብዬ የጮኽኩትን

ፍረድልኝ ብዬ ያልኩትን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ