Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማንም የለኝ

Manm Yelegn

2020 · ትራክ 4 · 9:07 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ማንም ሊፈታው አይችልም

ነገሬን ጉዳዬን ጌታ ሆይ (፪x)

አንተ ጋር መጣለው

ይዜው ነገሬን ጉዳዬን (፪x)

ፈቺ ነህ ጌታ ፈቺ ነህ

ፈቺ ነህ አንተ ፈቺ ነህ

ፍቅሩ ተፈትኖ ወርቅ ሆኖ ተገኝቶአል

በመከራ አልፎ ነፍሱን ለእኔ ሰጥቶአል

እራሱን አዋርዶ ፍቅሩን አሳይቷል

ከፍቅሮችም በላይ የእርሱ ፍቅር በልጧል

ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ

ስመላለስ በዚች ምድር ላይ

ነፍሱን ለእኔ ቤዛ ያደረገው

እውነተኛ ወዳጄ እርሱ ነው

ለህይወቴ ፍቺ ትርጉምን የሰጠው

ኑሮዬን አጣፍጦ እንዲህ ያደረገው

በእውነተኛ ፍቅሩ ያዳነኝ የመራኝ

ከኢየሱስ የሚበልጥ ለእኔ ማንም የለኝ

ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ

ስመላለስ በዚች ምድር ላይ

ነፍሱን ለእኔ ቤዛ ያደረገው

እውነተኛ ወዳጄ እርሱ ነው

ለክፉዎችም ቸር የሀጢያተኛ ወዳጅ

ከጥፋት ሚመልስ ለሰዎች የሚበጅ

ልብን የሚነካ ንግግሩ vጣፋጭ

እውነተኛ መሲሕ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ

ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ

ስመላለስ በዚች ምድር ላይ

ነፍሱን ለእኔ ቤዛ ያደረገው

እውነተኛ ወዳጄ እርሱ ነው

እኔ መኖር አልችል ስምህን ሳልጠራ

አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ (፪x)

እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ

አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ (፪x)

እኔ ማደር አልችል ስምህን ሳልጠራ

አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ (፪x)

እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ

አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ (፪x)

ያለምንም መኖር እችላለው

ደግሞም አይደልቀኝም ኖሬ አይቼዋለው

ግን ያላንተ ጌታ እንዴት እኖራለው

ግን ያላንተ ኢየሱስ እንዴት እኖራለው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ