Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መድሃኒቴ

Medhanite

2020 · ትራክ 6 · 4:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰዎች ተረዱልኝ እወቁት እወቁት

እርሱ ብቻ ነው የእኔ መድሐኒት

ሰዎች ተገንዘቡ እወቁት እወቁት

እርሱ ብቻ ነው የእኔ መድሐኒት

የእኔ መድሐኒት (፬x)

መድሐኒቴ እግዚአብሔር ነው

ይህን ሁሉ ያደረገው

ታዲያ ለእርሱ ምን እላለው

ምስጋናዬን አበዛለው

መድሐኒቴ መድሐኒቴ እግዚአብሔር ነው

ይህን ሁሉ ያደረገው

ታዲያ ለእርሱ ምን እላለው

አምልኮዬን አበዛለው

ክበር ብቻ

ተመስገን ብቻ (፪x)

ንገስ ብቻ

ከፍ በል ብቻ (፪x)

ክበር ብቻ

ተመስገን ብቻ (፪x)

ግነን ብቻ

ተመስገን ብቻ

ከፍ በል ብቻ

ይበቃሀል ወይ

ላንተ ላንተ ይህ አያንስም ወይ (፪x)

ይበቃሀል ወይ

ላንተ ላንተ ይህ አያንስም ወይ (፪x)

ሳስበው ፍቅሩን ሳስበው (፫x)

ለእግዚአብሔር ምስጋና አነሰው (፫x)

ሳስበው ማዳኑን ሳስበው (፫x)

ለእግዚአብሔር ምስጋና አነሰው (፫x)

አልቻልኩም ዝም ልል አልቻልኩም (፪x)

ፍቅሩ ይጎተጉተኛል

ተነሺ ዘምሪ ይለኛል

ማዳኑ ይጎተጉተኛል

ተነሺ አገልግይ ይለኛል

አልቻልኩም ዝም ልል አልቻልኩም (፪x)

ፍቅሩ ይጎተጉተኛል

ተነሺ አክብሪው ይለኛል

ማዳኑ ይጎተጉተኛል

ተነሺ አክብሪው ይለኛል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ