ሳይከፈል ባህሩ
Sayikefel Bahiru
2020 · ትራክ 2 · 4:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገና ሳይከፈል ባህሩ
ሳይሳካ ነገሩ (፪x)
እስቲ ላንሳ ከበሮውን
ላመስግነው እግዚአብሔርን (፪x)
አዝማች · Chorus
አመሰግናለሁ (፰x)
ዝም አልልም አመሰግናለሁ
ለጌታዬ ክብርን እሰጣለሁ
የጠላቴን ንዝነዛ እምቢ ብዬ
ላመስግነው ላክብረው ጌታዬ
አመሰግናለሁ (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁኔታ መጣና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ
ነገሮች መጡና ጠየቁኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አሉኝ
አዎ አመልካለው እባርከዋለሁ
አዎ አመልካለው ከፍ አደርገዋለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ
ክፉ ሁሉ ለጥሩ እንዲለወጥ
ይህንንም ጨምሬ አውቃለሁ
ስለዚህም አመሰግናለሁ
አመሰግናለሁ (፰x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁኔታ መጣና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ
ነገሮች መጡና ጠየቁኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አሉኝ
አዎ አመልካለው እባርከዋለሁ
አዎ አመልካለው ከፍ አደርገዋለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ