ነፍሴ አጥታልህ
Nefsie Atetaleh
2012 · ትራክ 6 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ
እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (፪x)
ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ
ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍቅርህ ልቤን ከነካው ከለወጠው
ሰንብቷል ያኔ ለጋ ሳለሁ
ከውስጠቴ ዘልቆ ገብቶ
ቤቱ አስቀረኝ ነፍሴን ማርኮ (፪x)
አዝማች · Chorus
ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ
እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (፪x)
ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ
ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፀጋህና ምህረትህ ለመዳኔ
ምክንያት ሆነኝ ለማምለጥ ከኩነኔ
በመስቀል ላይ በሰራኀው
ታላቅ ስራ እኖራለሁ
በመስቀል ላይ በሰራኀው
ታላቅ /ገድል ይሄው አለሁ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ
እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (፪x)
ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ
ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወደእግዚአብሔር የሚያደርሰው
እውነት ሕይወት መንገድ ኢየሱስ ነው
የሰው ልጅ በከንቱ እንዳይለፋ
ሁሉን ፈጸመ ሰጠውን ተስፋ
የዳነ ሰው ጌታ ያለው በማንነቱ
ከቶ አይደለም መወደዱ መመረጡ
ዓለም ገና ሳይፈጠር በክርስቶስ
የመረጠውን አጸደቀው አከበረው
ማንም እንዳይመካ በስራው አይደለም
ማንም እንዳይታበይ በስራው አይደለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ