የዜማ ጊዜ
Yeziema Gizie
2012 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘሩን ከእምባው ጋር የዘራ
እርኮ ተወስዶ የፈራ
ማሲንቆን አፍሮ የደበቀ
ጠላቱ ወድቆ ደቀቀ
ቡቃያ ደርሶ አፈራ
ወይኑ ዘለላው ጐመራ
በደስታ ነዶውን አጨደ
ማሲንቆውን አወረደ
አዝማች · Chorus
የጉብኝቴ ዘመን ፈጠነ
የዜማ ጊዜ እየደረሰ እንባዬ ታበሰ
ምርኮዬን መለሰ የልቤ ደረሰ
ቁጥር 2 · Verse 2
ድል አስታጠቀኝ አሄ ጠላት አፈረ (፪x)
ዳርቻዬን አሰፋልኝ ካዝማዬንም አጸናልኝ
ይሄው ቆመዋል አግሮቼ ምርኩዝ ሆኖልኝ አባቴ
ተሰብሯል የሃፍረት ቀንበሬ ሞልቶታል አፌን ዝማሬ
ሞገስ በረከት ከደጅ ገብቷል ኢየሱስ ወዳጄ
አዝማች · Chorus
የጉብኝቴ ዘመን ፈጠነ
የዜማ ጊዜ እየደረሰ እንባዬ ታበሰ
ምርኮዬን መለሰ የልቤ ደረሰ
ቁጥር 3 · Verse 3
ድል አስታጠቀኝ እሰይ/አሜን ጠላት አፈረ (፪x)
ነፍሴ ሆይ ደስ ይበልሽ
ለምሥጋና ደግሞ ተነሽ
አጥንቶቼ እግዚአብሔርን ባርኩ
ታላቅ ስሙን በሉ አወድሱ
አካላቶቼ በድል ዘምሩ
በነጋ ጠባ ስራውን አብስሩ
ያላሳፈረኝ ሞገስ የሆነኝ
ጌታ ነውና ዛሬም ያገዘኝ
በምሥጋን (፫x) ልቤ ተነሳ
በምሥጋን (፫x) መጣሁ እንደገና
በምሥጋና (፫x) ድል አለ እንደገና
ልቤ በሃሴት በደስታ
ፈሰሰ ቀኔ ዕልልታ
ከአለት እቃቃት ወጥቼ
ድምጼን ላሰማ ለአምላኬ
ጭጋጉ ይሄው ገፈፈ
ሀዘን ትካዜው አለፈ
ላሞግሰው እንደገና
በድል ዝማሬ ምሥጋና
አዝማች · Chorus
የጉብኝቴ ዘመን ፈጠነ
የዜማ ጊዜ እየደረሰ እንባዬ ታበሰ
ምርኮዬን መለሰ የልቤ ደረሰ
ቁጥር 4 · Verse 4
ድል አስታጠቀኝ እሰይ/አሜን ጠላት አፈረ (፪x)
ነፍሴ ሆይ ደስ ይበልሽ
ለምሥጋና ደግሞ ተነሽ
አጥንቶቼ እግዚአብሔርን ባርኩ
ታላቅ ስሙን በሉ አወድሱ
አካላቶቼ በድል ዘምሩ
በነጋ ጠባ ስራውን አብስሩ
ያላሳፈረኝ ሞገስ የሆነኝ
ጌታ ነውና ዛሬም ያገዘኝ
በምሥጋን (፫x) ልቤ ተነሳ
በምሥጋን (፫x) መጣሁ እንደገና
በምሥጋና (፫x) ድል አለ እንደገና
በምሥጋን (፫x) ልቤ ተነሳ
በምሥጋን (፫x) መጣሁ እንደገና
በምሥጋና (፫x) ድል አለ እንደገና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ