በምወደው ዜማ
Bemewedew Zeima
2012 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምሥጋና ልሰዋ በተዋበ ዜማ
ሁሉ በሚቀለው ሊዘምር ከእኔ ጋር
ደስ ብሎኝ ተነሳሁ ልመታ ከበሮ
አምላኬ አርቆታል የልቤን እሮሮ
አዝማች · Chorus
(ኦሆኦሆሆ) ደስ ያለው ይዘምር
ቁጥር 2 · Verse 2
(ኦሆኦሆሆ) ተሰብሮለት ቀንበር
(ኦሆኦሆሆ) ይሰዋ ምሥጋና
(ኦሆኦሆሆ) ለጌታ እንደገና
ላከበረኝ ጌታ በምወደው ዜማ
በሚገባኝ ቋንቋ ቅኔን በሙገሳ
ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ
በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ
የባርያዪቱን ውርደት አምላኳ አየና
ስድብ ነቀፋዋን አስቦ እንደገና
እግዚአብሔር ከሰማይ ቀንን ሲቆጥርላት
መገፋቷን አይቶ ዛሬ ደረሰላት
ቀንዴ ከፍ ብሏል አፌም ይዘምራል
ጓዳዬ በቅኔ በዝማሬ ደምቋል
አዝማች · Chorus
(ኦሆኦሆሆ) ደስ ያለው ይዘምር
ቁጥር 3 · Verse 3
(ኦሆኦሆሆ) ተሰብሮለት ቀንበር
(ኦሆኦሆሆ) ይሰዋ ምሥጋና
(ኦሆኦሆሆ) ለጌታ እንደገና
ላከበረኝ ጌታ በምወደው ዜማ
በሚገባኝ ቋንቋ ቅኔን በሙገሳ
ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ
በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ
የእንባ ስቅታዬ መርዶ በወጣበት
ዛሬ ግን ከቤቴ ምሥጋናን ሞላበት
አምላኬ በክብሩ ወደ እልፍኜ ገብቷል
የዕልልታዬ ድምጽ ከሩቁ ይጠራል
ወዳጅ ዘመዶቼ ጌታ ይሰራልኝን
አይተው ከእኔ ጋራ አከበሩት ውዴን
አዝማች · Chorus
(ኦሆኦሆሆ) ደስ ያለው ይዘምር
ቁጥር 4 · Verse 4
(ኦሆኦሆሆ) ሆኖ ከእኒ እጋራ
(ኦሆኦሆሆ) የተደረገለት
(ኦሆኦሆሆ) እስቲ ማን አለና
ላከበረኝ ጌታ በምወደው ዜማ
በሚገባኝ ቋንቋ ቅኔን በሙገሳ
ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ
በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ
ልስገድ በሽብሸባ ይጨመር ጭብጨባ
ይህ አይበቃምና መቅደስ ውስጥ ስገባ
ምቱልኝ ከበሮ የታለ ዕልልታ
በማዕረግ መዝሙር ላክብረው በሆታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ