ቀን ሳለ
Qen Sale
2012 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀድሞ ወፉ ሳይጮህ ጠዋት በማለዳ
ጌታ ፈጥኖ መጣ ልጆቹን ሊያነቃ
ማን ይላከኝ ብሎ ስራውን ሊሰራ
እጣውን ለወደደው ተሰጠው አደራ
ዓለም ቀውጢ ሆና እጅግ ተጨንቃለች
በል ስጣት መድሃኒት ፈውስ አታተማለች
ፍጠን ልጄ አለው ሳይመሽብህ ቀኑ
መርቆ ሰደደው እንዲቀና መንገዱ
ቢነቃም ማለዳ እጅ እግሬን እያለ
ከቤቱ የወጣው አርፍዶ ነበረ
ከመንገዱ ሳለ ገና ሳያጋምስ
ጠለቀበት ጀምበር ከቦታው ሳይደርስ
መራመድ ቢጀምር ብርሃኑ ጨላልሞ
ተሰብሮ ወደቀ መልዕክቱን አንግቦ
ምን ሊጠቅመው ታዲያ በጸጸት መንደዱ
መሮጡ በበጀው ብሩህ ሳለ ቀኑ
አዝማች · Chorus
ቀን ሳለ ልሩጥ ሳይጨልም ብርሃኑ
ሳይመጣ ጽልመቱ ሳይዘኝ ድባቡ
(ልሩጥ) ወገግ ሲል ቀኑ
(ልሩጥ) ሳይጠልቅ ጀምበሩ
(ልሩጥ) ሳይደክም ጉልበቴ
(ልሩጥ) ሳይዝል ሰውነቴ
ሳይደክም (ልሩጥ) ጉልበቴ
ሳይዝል ሰውነቴ
ሳይመጣ (ልሩጥ) ጽልመቱ
ሳይዘኝ ድባቡ
ቁጥር 2 · Verse 2
ትንፋሽ ያለው ፍጥረት መሽቶለት ሲነጋ
አለው ብዙ ተግባር ዛሬን እንዲተጋ
አለው ብዙ ልፋት አለው ብዙ ጥረት
ነገም ሌላ ቀን ነው ሌላ ደግሞ ሂደት
ሳይተጉበት ዛሬ ሳይኖሩ ለዛሬ
አንዳች ሳይጨበጥ ሲገፋ ያ ዕድሜ
ምን ሊፈይድ ታዲያ በጸጸት መንደዱ
መሮጡ ይበጃል ምቹ ሳለ ቀኑ
አዝማች · Chorus
ቀን ሳለ ልሩጥ ሳይጨልም ብርሃኑ
ሳይመጣ ጽልመቱ ሳይዘኝ ድባቡ
(ልሩጥ) ወገግ ሲል ቀኑ
(ልሩጥ) ሳይጠልቅ ጀምበሩ
(ልሩጥ) ሳይደክም ጉልበቴ
(ልሩጥ) ሳይዝል ሰውነቴ
ሳይደክም (ልሩጥ) ጉልበቴ
ሳይዝል ሰውነቴ
ሳይመጣ (ልሩጥ) ጽልመቱ
ሳይዘኝ ድባቡ
ቁጥር 3 · Verse 3
"እራሱን የሚወቅስ እራሱንም ሚዘልፍ
ስንቱ ነው በቤቱ እለት በእለት ሲያልፍ
ዛሬ የትላንት ውጤት መሆኑ ሚገባው
አንዳንዱ ዘግይቶ በረፋዱ ላይ ነው
እንግዲያው በቀረው በተረፈው ዘመን
ኋለእኛው ይበርታ ሊበቀል ትናንትን
የወደቀ ይነሳ ራዕዩ ያድስ
ሃይልን በሚሰጠው በእግዚአብሔር መንፈስ"
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ