አውቃለሁ
Awqalehu
2012 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ግራና ቀኜን ከፊት ከኋላ
ሲጨልምብኝ ባጣ ማረፊያ
ተስፋዬ ያልኩት በእጄ ይዤ
ድንገት ሲከዳኝ ብቀር ተክዤ
የተውከኝ ሲመስለኝ አምላኬ ከላይ
ምድር ጐርብጣ ቢዘጋ ሰማይ
አሃሃ አውቃለሁ
አንተ ሁልጊዜ ትክክል እንደሆንክ
አውቃለሁ ተናግረህ ማትፈጽም ቀላባይ እንዳልሆንክ
አዝማች · Chorus
አውቃለሁ ለእኔ መልካም ሃሳብ እንዳለህ
ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ
ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሀጥያቴ ሲጋለጥ ለአሉታ ወሬ
በነበር ሆኖ ሳይቀር ነገሬ
የሽንፈት ቃላት ከአፌ እንዲወጣ
ሲወተውተኝ ምክንያት ቢያጣ
ሙሾ ሲደረድር ይኸው ጠፋሁ ብዬ
በገናዬን ስጥል ሊስቅ ባላንጣዬ
አሃሃ አውቃለሁ ዞርበል አንተ ክፉ ብሩህ ቀን አያለሁ
አሃሃ አውቃለሁ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው አመሰግናለሁ
አዝማች · Chorus
አውቃለሁ ለእኔ መልካም ሃሳብ እንዳለህ
ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ
ፍቅር ነው አላማህ በእኔ ላይ ውዴ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ልዩ ነህ
ፍቅር ነህ
በእኔ ላይ አላማህ ልዩ ነው
ልዩ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ