እምነት
Emnet
2012 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ብዙ እንቆቅልሽ አሄሄ
ዛሬም ከብዶባቸው
ዘወትር በልማድ ከበራፉ ደርሰው
ይመጣሉ ይገባሉ ተቀምጠው ይወጣሉ
ያመነ ሰው ሲድን ያዩ
ምታስበኝ መች ነው ይላሉ
ጌታ እንደሚችል አፋቸው ቢያወራ
ልባቸው ቢፈተሽ አሄሄ
ጥቂት እምነት የለም
በጥርጣሬ እምነታቸው ጐድሎ
ሁሉን ቻዩ ጌታ ከእነርሱ ጋር ውሎ
ከነጥያቄያቸው ተመልሰው ሄዱ
ትላንት የሚደክሙ አሃሄሄ"
ለአመታት በሃፍረት ከሰው ያገለላት
ወዳጅ አልባ ሆና ብቻዋን ያስቀራት
ለህመሟ መድሃኒት መፍትሄ ሲጠፋ
በልቧ ስትጠብቅ ኢየሱስን በተስፋ
ቀሚሱን በእምነት ብትነካ በእጆቿ
እንደ እምነቷ ሆነ ሀይል ከእርሱ
የበሽታው ምንጭ ከስሩ ደረቀ
በሰውነቷ ላይ መዳኗ ታውቀ
አዝማች · Chorus
(ለሚያምን) ኧረ ሁሉ ይቻላል
(ለሚያምን) ቀሚሱ ያድናል
(ለሚያምን) ቃሉ ይፈውሳል
(ለሚያምን) ኢየሱስ ያድናል
ቁጥር 2 · Verse 2
እምነት በመስማት ነው መስማትም በቃሉ
እግዚአብሔርን ማወቅ ይበልጣል ከሁሉ
ኤልሻዳይ ሁሉን ቻይ የሆነውን ጌታ
እንዳይችል አሰብነው ሆነን በልብታ
እግዚአብሔር እራሱ እንዲሆን ቢነግረን
ማመን ይሳነናንል ከቃሉ ርቀን
አዝማች · Chorus
(ለሚያምን) ኧረ ሁሉ ይቻላል
(ለሚያምን) ቀሚሱ ያድናል
(ለሚያምን) ቃሉ ይፈውሳል
(ለሚያምን) ኢየሱስ ያድናል
ቁጥር 3 · Verse 3
ባሪያዬ በጠና ታሞ ከቤቱ ላይ ውሏል
በቃልህ እዘዝ ብቻ ካልጋ ላይ ይነሳል
ከጣሪያዬ በታች ልትገባ አይገባህም
ተናገረኝ እንጂ ይህ ቀን አያልፈኝ
ጌታም ተደነቀ በዚህ ሰው እምነት
ብላቴናው ድኗል ሂድ ወደቤትህ
አለው ኤልሻዳዩ ሁሉ የሚቻለው
ቃሉን ሰደደና ባሪያውን ፈወሰው
አዝማች · Chorus
(ለሚያምን) ኧረ ሁሉ ይቻላል
(ለሚያምን) ቀሚሱ ያድናል
(ለሚያምን) ቃሉ ይፈውሳል
(ለሚያምን) ኢየሱስ ያድናል
ቁጥር 4 · Verse 4
እምነት በመስማት ነው መስማትም በቃሉ
እግዚአብሔርን ማወቅ ይበልጣል ከሁሉ
ኤልሻዳይ ሁሉን ቻይ የሆነውን ጌታ
እንዳይችል አሰብነው ሆነን በልብታ
እግዚአብሔር እራሱ እንዲሆን ቢነግረን
ማመን ይሳነናንል ከቃሉ ርቀን
ቁጥር 5 · Verse 5
(ለሚያምን) ጨለማው ይበራል
ቁጥር 6 · Verse 6
(ለሚያምን) ብበሩ ይከፈታል
(ለሚያምን) ተራራው ይናዳል
(ለሚያምን) በእምነታችን ጌታ እንዴት ደስ ይለዋል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ