ጥበበኞችን ሊያሳፍር
Tebebegnochen Liyasafer
2010 · ትራክ 7 · 4:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው ሰውን ይወዳል ይቀርባል ለጥቅሙ
ቢጤውን ፈልጐ እንዳሳቡ
እኔን ግን የገረመኝ የደነቀኝ
አዝማች · Chorus
እ/ር ወዶኛል እንዲሁ እንዲሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተሰማ ምስራቹ ሜዳ ባደሩ በእረኞቹ
ወንጌሉ ተሰበከ ባልተማሩ ዓሣ አጥማጆች
ቢሉትም ግብዞቹ ያሃጢያተኞች ዋና ወዳጅ
እልቀረም ሳይማርከው ያንን ባዩን ያን አሳዳጅ
ጥበበኞችን ሊያሳፍር ያለምን ደካሞች መረጠ
የከበሩትን ሊያሳፍር ምናምንቴዉን አከበረ
ይሄው የዓለም ቤዛ ያለም ንጉስ ቤቴ ገባ
ከእኔ ጋር እራት ሊቆርስ በረከቱን ሊያፈስስ
ደካሞችን ሲጠራ ለእኔም ደርሶኛል ጥሪው
ፈልጐ ከመረጠ ለምን አይባል ምርጫው
አዝማች · Chorus
ጥበበኞችን ሊያሳፍር ያለምን ደካሞች መረጠ
የከበሩትን ሊያሳፍር ምናምንቴዉን አከበረ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታን ሳገለግል በምን ጥሩ ጐኔ
እንዲህ ነው የምለው ታሪክ የለኝ እኔ
መረጠኝ ወደደኝ ፈለገኝ መድህኔ
አዝማች · Chorus
እንዲሁ እንዲሁ ከነምኔ ከነምኔ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ