ረድኤቴ
Redietie
2010 · ትራክ 4 · 4:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዓይኖቼን አነሳሁ ወደ ተራሮቹ
ይረዱኝ እንደሆን ብዬ ትልቆቹ
ታግሼ ጠበኩኝ የቃል ተስፋቸውን
ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሳይ እጅ እጃቸውን
ክረምት አልፎ በጋ ይኸው መጣ
ረዳቴ ግን ከየት ከየት ይምጣ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ጌታዬ አድነኝ
በደጅህ መጣሁኝ መረጥኩኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ረድኤቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው
ሰማይን ምድርን ከሰራው (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ደግ ነው አያሳፍርም
ይረዳኛል አምናለሁ አያሳፍርም
የጨለመ ቢመስልም አያሳፍርም
ጌታ ይመጣል አይቀርም አያሳፍርም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዓይኖቼን ቀና አድርጌ ያልከኝን አስታውሳለሁ
መከራዬን ሀዘኔን ያን ጊዜ እረሳዋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እዛ ጋር አለው ዋጋ (፪x)
አንተ ጋር አለው ዋጋ
እዛ ጋር አለው ዋጋ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ