Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዘላለማዊ

Zelalemawi

2010 · ትራክ 11 · 3:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላኬ ሆይ ለስምህ ዘምራለሁ ምሥጋናህ በአፌ ነው

በማለዳ ምህረትህን በሌሊትም እውነትህን አወራለሁ

በእጣ ክፍሌ ስለቆምኩ በፊትህ ክብርህን እንዳወራ

አጥናለሁ ሁልጊዜ የመረጥከኝም አንተው ነህ ለዚህ ስራ (፪x)

እስካልወሰድክብኝ እስካለ እስትንፋሴ እስካለ እስትንፋሴ

አቀርብልሃለሁ የነፍሴን ውዳሴ የነፍሴን ውዳሴ (፪x)

ክበርብኝ ክበርብኝ

ንገሥብኝ ንገሥብኝ (፪x)

ዓመታቶችህ አያልቁምና (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ)

የዕድሜ መነሻ መጨረሻ (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ)

የፍጥረት ንጉሥ የፍጥረት ጌታ (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ)

ይሰማ ለአንተ በኩር ምሥጋና (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ) (፪x)

አንተ ጥንትም ነበርክ ዛሬም አለህ

ለዘላለም ትኖራለህ ተከብረህ/ነግሰህ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ