Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅር ነው

Feqer New

2010 · ትራክ 12 · 4:35 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተጨነቀ ተሰቃየ

አፉን አልከፈተም ዝም አለ

ታረደ እንደ በግ

የእኔን ነፍስ ሊታደግ

የእኔን ነፍስ ሊታደግ

ተጨነቀ ተሰቃየ

አፉን አልከፈተም ዝም አለ

ታረደ እንደ በግ

የእኔን ነፍስ ሊታደግ

የእኔን ነፍስ ሊታደግ

ሁሌ አስባለሁ ፍቅሩን

ሁሌ እስበዋለሁ ፍቅሩን

የኢየሱሴን የእውነተኛውን

ሁሌ አስባለሁ ፍቅሩን

ሁሌ እስበዋለሁ ፍቅሩን

የኢየሱሴን የእውነተኛው

የህማም ሰው ሆነ በደዌ ተመታ ፍቅር ነው

እንደ በግ ተነድቶ እንዳልሆነ ጌታ ለእኔ ነው

እሾሁን ጅራፉን እለፋውን ቻለ ፍቅር ነው

መስቀል ተሸክሞ ደፋ ቀና እያለ ለእኔ ነው

የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእጁ ሊከውን

ከነፍሱ ድካም ሊያይ ብርሃንን

ታግሶታል አቤት ኢየሱሴ

በጸሎት በእንባ ታክብረው ነፍሴ

ጌታ እሰከሞቱ ሰው ወደደ

ጌታ እስከ መስቀል ሞት ሰው ወደደ

ይቅር በላቸው በሎ እየማለደ

ጌታ እሰከሞቱ ሰው ወደደ

ጌታ እስከ መስቀል ሞት ሰው ወደደ

ይቅር በላቸው በሎ እየማለደ

ኤሎሄ ኤሎሄ እያለ ተጣራ ፍቅር ነው

እንደማይችል እራሱን ባዶ አደረገና ለኔ ነው

እንደ ወንጀለኛ እየተዘለፈ ፍቅር ነው

ስለ ሃጥያተኞች ነፍሱን አሳለፈ ለኔ ነው

የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእጁ ሊከውን

ከነፍሱ ድካም ሊያይ ብርሃንን

ታግሶታል አቤት ኢየሱሴ

በጸሎት በእንባ ታክብረው ነፍሴ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ