ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
Tezetayie Qaleh Yehun
2010 · ትራክ 3 · 4:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ
እንዲሆን የሞገስ ዘውዴ የአንገት ድርዬ
ሁሌ ቃልህ ነውና የእግሬ መብራት
መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤቱ እንዳልበድልህ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
መንገድም እንዲነጻልኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
በትዕዛዝህ መንገድ እንድሮጥ
ተንሸራትቼም እንዳልገባ ማጥ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ስንፍናን ተግቼ ኃጢአትን ሳላምጥ
ሕይወቴ በድንገት እንዳያመልጥ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ቁጥር 3 · Verse 3
ስህተትን እንዳስተውላት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
እንድሰወር ከስውር ኃጢአት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ከጓደኞቼ ጋር በሳቅ ጨዋታ
መስመር እንዳላልፍ እንዳልረሳ ጌታ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
የድፍረት ኃጢአት ጠፍሮ እንዳይዘኝ
የቃልህ ፍርሃት ሁልጊዜ እንዲያዘኝ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
አዝማች · Chorus
ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
መፅናናት ሲያስፈልገኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
መከራው ሲያሳድደኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ከጠላቴ ዛቻ ከምክሩ እንዳልፈራ
ልቤ እንዲጠበቅ በምክርህ እንድመራ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
የኃጥአን ገመዶች ሲተበተቡብኝ
አለቆች ተቀምጠው ሲያሙኝ
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
በአመፀኞች እንዳልቀና ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
የግፍ እንጀራ እንዳልበላ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
ቁጥር 5 · Verse 5
የጓዳዬን ኑሮዬን ቤቴን ለመሙላት
በከንፈሬ እንዳልወሰልት
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
እግሬ እንዲከለከል ከክፋት ጐዳና
በፈተና ሁሉ እምነቴ እንዲፀና
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን
አዝማች · Chorus
ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ
እንዲሆን የሞገስ ዘውዴ የአንገት ድርዬ
ሁሌ ቃልህ ነውና የእግሬ መብራት
መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ