በእግዚአብሔር ምህረት
Begziabhier Meheret
2010 · ትራክ 1 · 4:29 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ለምን እሩቅ ልሂድ ለምን ጐረቤቴ
ፍቅርህን ካየሁት አለሁበት እኔ
የፍቅርህ ምሳሌ የመውደድህ ምሳሌ
አለሁኝ እኔ
የማክበርህ ምሳሌ የማንሳትህ ምሳሌ
አለሁኝ እኔ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ምህረትህን አልከለከልከኝም
በጠላት እጅ አልዘጋህብኝም
ሆነህልኝ የመጠጊያ ቤቴ
እረሳሁት ሃዘኔን ምሬቴን
ተከተለኝ ቸርነት ምህረትህ
ጨመረልኝ የሕይወት ውበት
በፍቅርህ ከመደነቅ በቀር
ምን ልበል ምን አለ ሌላ ነገር
አዝማች · Chorus
ለምን እሩቅ ልሂድ ለምን ጐረቤቴ
ፍቅርህን ካየሁት አለሁበት እኔ
የፍቅርህ ምሳሌ የመውደድህ ምሳሌ
አለሁኝ እኔ
የማክበርህ ምሳሌ የማንሳትህ ምሳሌ
አለሁኝ እኔ
ቁጥር 2 · Verse 2
ባትመግበኝ እጅህ ምህረትህ
እጠፋለሁ ከዓይንህ በቅፅበት
የምህረትህ ጥገኛ ናት ነፍሴ
ታስፈልገኛለህ እንደ እስትንፋሴ
አዘነብከው ፍቅርህን በላዬ
አረሰረሰኝ ዘልቆ በጓዳዬ
አያልቅብህ አንተስ ደግነት
የትልቅ የትንሹ አባት
ይነበብ ይነበብ ታሪኬ
ይነገር በእኔው አፍ (፪x)
በእግዚአብሔር ምህረት ተወልጄ
በእግዚአብሔር ምህረት ታድጌያለሁ
በእግዚአብሔር ምህረት ሮጬ ሮጬ
በእግዚአብሔር ምህረት እሄዳለሁ (፫x)
በእግዚአብሔር ምህረት ተወልጄ
በእግዚአብሔር ምህረት ታድጌያለሁ
በእግዚአብሔር ምህረት ሮጬ ሮጬ
በእግዚአብሔር ምህረት እሄዳለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ