Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ያሻግራል ማዶ

Yashageral Mado

ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከቁጥር አለፈ በዛ (፪x) ምህረቱ

ተዐምራቱን አየሁ በዐይኔ (፪x) በየዕለቱ

አምላኬ አቤቱ (፬x) ብዙ ተዐምራቱ

ሚሳሳልኝ የሚወደኝ ነፍሴም የምትወደው

የልቤ አምላክ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ እኮ ነው

ምህረቱ ቸርነቱ ይከታተሉኛል

የእግዚአብሔርን ብርቱ ፍቅር እንዳይ ያደርጉኛል አዎ

ሆሆ እባርከዋለሁ (፪x) ነፍሴን አፈስለታለሁ አዎ

ከቁጥር አለፈ በዛ (፪x) ምህረቱ

ተዐምራቱን አየሁ በዐይኔ (፪x) በየዕለቱ

አምላኬ አቤቱ (፬x) ብዙ ተዐምራቱ

ፍቅሩ ብዙ ቸሩ ጌታ ጊዜ የማይለውጠው

ሁኔታዎች ማያግዱት እኔስ እርሱን አየሁ

ሺ አንደበት አይገልጸውም የእርሱን ውለታ

ብሰዋለት ምሥጋናዬን ዛሬም በደስታ

ሆሆ እባርከዋለሁ (፪x) ነፍሴን አፈስለታለሁ አሃ

ምሥጋና (፫x) ምሥጋናዬ

ለባለውለታዬ አሃሃሃ ታብሶልኛል እምባዬ አሃሃሃ

ለባለውለታዬ አሃሃሃ ተከፍሎልኛል ዕዳዬ አሃሃሃ

ያሻግራል ማዶ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ውዴ ያሻግራል

ታሻግራል ማዶ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ሁሉን ያሻግራል

ተሻገርኩት እኔስ በምሥጋና ፤ አየሁኝ ክንዶቹን እንደገና

አምላኬ ገናና (፭x)

ታላቁን ቀይ ባሕር በድንቅ የከፈለ

ህዝቡን በተዐምር በድል ያሻገረ

ያ የቀድሞው ክንዱ መቼ ደከመና

አየሁኝ ሲያሻግር ህዝቡን በምሥጋና (፪x)

ያሻግራል ማዶ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ውዴ ያሻግራል

ታሻግራል ማዶ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ሁሉን ያሻግራል

ተሻገርኩት እኔስ በምሥጋና ፤ አየሁኝ ክንዶቹን እንደገና

አምላኬ ገናና (፭x)

አስፈሪውን ማዕበል በስልጣን አዘዘው

የሚናወጠውን ወጀብ ጸጥ አደረገው

እኔም አመለጥኩኝ በክንዶቹ ብርታት

ልውደቅ በእግሮቹ ስር እጥፍ ልስገድለት

አሃ ይህም አነሰበት

ያሻግራል ማዶ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ውዴ ያሻግራል

ታሻግራል ማዶ ያሻግራል ፤ ያሻግራል ሁሉን ያሻግራል

ተሻገርኩት እኔስ በምሥጋና ፤ አየሁኝ ክንዶቹን እንደገና

አምላኬ ገናና (፭x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ