ማደሪያህ ድንቅ ነው
Maderiyah Denq New
ትራክ 6 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የሰራዊት አምላክ ሆይ
ማደሪያህ እንዴት ድንቅ ነው
ማደሪያህ እንዴት ልዩ ነው
ማደሪያህ የተወደደ ነው አዎ (፪x)
ነፍሴ አንተን አደባባዮችህ
ወደደችህ አሃሃሃ ወደደችህ አዎ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አእላፋት መላእክት በፊትህ
ቅድስናህን ሚያውጁልህ
ዙፋንህ ቅዱስ ነው ገናና
በምሥጋናም የተፈራህ
ድምጽህ እንደብዙዎች ነው
ቃልህ ከማር እልቅ ጣፋጭ ነው
በምክርህ ግሩም ነህ ጌታዬ
ዙፋኑ የአንተ ነው የልቤ
በምክርህ ግሩም ነህ ጌታዬ
ዛሬም ሾሜሃለሁ በላዬ
አዝማች · Chorus
የሰራዊት አምላክ ሆይ
ማደሪያህ እንዴት ድንቅ ነው
ማደሪያህ እንዴት ልዩ ነው
ማደሪያህ የተወደደ ነው አዎ (፪x)
ነፍሴ አንተን አደባባዮችህ
ወደደችህ አሃሃሃ ወደደችህ አዎ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤቱ ውበትህ ያማረ
እኔስ አላየሁም እንደአንተ
ፍጥረት ተደነቀ በስራህ
አቤት የእኔስ ጌታ ልዩ ነህ
በትንሿ ልቤ ገብተሃል
ማደሪያ ቤትህ አድርገሃል
አኔም ሁልጊዜ ላምልክህ
ኢየሱስ ጌታዬ ልበልህ
እኔም ሁልጊዜ ላክብርህ
ኢየሱስ ጌታዬ ልበልህ
ኢየሱሴ ጌታዬ አምባዬ ጋሻዬ
እውነተኛ ወዳጅ እንደአንተ ማነው
በጨለማው ሌሊት ፈጥኖ ሚደርሰው
ነፍሴ አንተን ባርኮ አጸለችም
ክበር የእኔ ጌታ ለዘለዓለም (፪x)
አምላኬ አሃ ያደረከው ነገር ለእኔ
የሰራኸው ስራ በዘመኔ
ቢነገር ቢነገር ስጦታህ
መች ያልቃል ጌታዪ ደግነትህ
መች ያልቃል አባትዬ ደግነትህ
ባወራው ባወራው ስጦታህን
መች ያልቃል ኢየሱስዬ በጐነትህ
መች ያልቃል ወዳጄ በጐነትህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ