ጽኑ ነው መሰረቴ
Tsenu New Meseretie
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጽኑ ነው መሰረቴ ዐይናወጥ አለቴ
አምባ ነው ለእኔስ መድሃኒቴ (መድሃኔቴ ኢየሱስ)
እኔስ ክፉን አልፈራም ጐርፉም አያሰጋኝም
ተተክያለሁ ለዘለዓለም (፪x) አው
በአደባባዩ ለዘለዓለም (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የማይናወጥ ጽኑ መሰረት
ኢየሱስ አለኝ የማዕዘን?? አዎ??
ከቶ አልሰጋም ሁሉ በከፋ
ቃሉ አያረጅም አለኝ ተስፋ
ምርኩዝ መጠጊያ ላዘመሙት
ጽናት ይሆናል ለደከሙት (፪x)
አዝማች · Chorus
ጽኑ ነው መሰረቴ ዐይናወጥ አለቴ
አምባ ነው ለእኔስ መድሃኒቴ (መድሃኔቴ ኢየሱስ)
እኔስ ክፉን አልፈራም ጐርፉም አያሰጋኝም
ተተክያለሁ ለዘለዓለም (፪x) አው
በአደባባዩ ለዘለዓለም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መልካም ኧረና ቤዛ ለዓለም
በቤቱ ተክሎ የሚያለመልም
እርሱ እያለልኝ ምን ያሰጋኛል
ዘለዓለም ቤቱ ያኖረኛል
ምርኩዝ መጠጊያ ላዘመሙት
ጽናት ይሆናል ለደከሙት (፪x)
አዝማች · Chorus
ጽኑ ነው መሰረቴ ዐይናወጥ አለቴ
አምባ ነው ለእኔስ መድሃኒቴ (መድሃኔቴ ኢየሱስ)
እኔስ ክፉን አልፈራም ጐርፉም አያሰጋኝም
ተተክያለሁ ለዘለዓለም (፪x) አው
በአደባባዩ ለዘለዓለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አለት ላይ ያጸና ያን ቤቱን
ያነጸ ያን ቤቱን (በኢየሱስ ላይ)
እርሱ ነው ልባም ሰው በእውነቱ
ልባም ሰው በእውነቱ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ