ቸርነትህን አዜማለሁ
Cherenetehen Aziemalehu
ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ፤ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ
ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን አዜማለሁ
አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ
አባቴ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተስፋ ያደረኩት ያመንኩት ሲከዳኝ
አስፈሪው ጨለማም ዙሪያዬን ሲከበኝ
ነፍሴ ስትጨነቅ ደረስህ ወዳጄ
ጨለማዬም በራ ተዋበልኝ ደጄ
ላንግስህ ሰግቼ ኢየሱስ ላንግስህ ሰግቼ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ፤ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ
ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን አዜማለሁ
አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ
አባቴ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ
ቁጥር 2 · Verse 2
የተሰበረውን ስብራቱን ጠጋኝ
የታመመን ፈዋሽ ያዘነውን አጽናኝ
ከእናት ከአባት በላይ ደርሰህ ትረዳለህ
የምስኪኑ አባት መጠጊያው አንተ ነህ
ዛሬም ላሞጋግስህ ኢየሱስ ዛሬም ላሞጋግስህ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ፤ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ
ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን አዜማለሁ
አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ
አባቴ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ
ቁጥር 3 · Verse 3
ወደላይ ብወጣም አንተ በዚያ አለህ
ወደታች ብወርድም በዚያም ትገኛለህ
በምድር ስፋት ሁሉ ያለውን የምታይ
እንደአንተ ማን አለ የሚኖር በሰማይ
አንተ ነህ የበላይ ጌታ አንተ ነህ የበላይ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ፤ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ
ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ፤ ቸርነትህን አዜማለሁ
አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ
አባቴ አንተን የእኔ ጌታ ፤ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ