ኢየሱሴ እንደ አንተ ያለ
Eyesusie Ende Ante Yale
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መከራ ሲበዛ ቀንም ሲጨላልም
ኢየሱስ አንተ ነህ የምትሆን ወንድም አዎ
የተዘጋውን በር ደርሰህ ትከፍታለህ
ከድሃው ጐን ኢየሱስ ትቆምለታለህ አዎ
የምስኪኖች ወዳጅ ኢየሱስ የተጣለን ምታነሳ
ቸር አምላክ??? በክብር ምታኖር አበሳውን ምታስረሳ
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ጌታዬ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት)
አቤት አቤት አባባ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተው ብቻ አባቴ ነህ አንተው ብቻ ጌታ
አንተው ብቻ ወዳጄ ነህ አንተው ብቻ ጌታ
አንተው ብቻ አሃሃ አንተው ብቻ አዎ
አንተው ብቻ እውነተኛ አንተው ብቻ ኢየሱስ
ቁጥር 3 · Verse 3
ዘመን ቢከፋም እኔስ አምንሃለሁ
አንተ እኮ ከያዝከኝ እንዳልወድቅ አውቃለሁ አዎ
የማምለጫ አለት መሸሻ አምባዬ
የክፉ ቀን ወዳጅ ለእኔስ መጠጊያዬ አዎ
ዝርግፍ ጌጤ ምኮራብህ አለኝ ብዬ ምመካብህ
አንተው ብቻ የእኔ ወዳጅ በራሴ ላይ ዛሬም ሾምኩህ
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ኢየሱሴ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት)
ቁጥር 4 · Verse 4
አቤት አቤት አባቴ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ
አንተው ብቻ መኩራዬ ነህ አንተው ብቻ ጌታ
አንተው ብቻ ዝርግፍ ጌጤ አንተው ብቻ ጌታ
አንተው ብቻ አሃሃ አንተው ብቻ ኢየሱስ
አንተው ብቻ እውነተኛ አንተው ብቻ ኢየሱስ
ቁጥር 5 · Verse 5
ሰባራውን ልቤን አንተው ጠገንክልኝ
ሸክሜን ከላይ አንከባለልክልኝ አዎ
ዛሬ ይኸው ቀና አልኩኝ በአንተ የእኔ ጌታ
አርነት ወጣሁኝ መቆዘኔ አበቃ አዎ
የልቤ ወዳጅ ሚስጥረኛ የጓዳዬን ምታውቅልኝ
አቤት በአንተ ስንቱን አለፍኩ ኢየሱሴ ክበርልኝ
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ጌታዬ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት)
አቤት አቤት አባባ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ
ቁጥር 6 · Verse 6
በመከራዬ ቀን ለቅሶዬን ሰምተሃል
እምባዬን አብሰህ ሳቅ አርገህልኛል
አስጨናቂዎቼ ዛሬ ይኸው አፈሩ
አንተ የሰራኸውን ማዳንህን አዩ አዎ
ማን እንደአንተ የእኔ ኢየሱስ እስራትን የሚፈታ
ቀንበር ሰብሮ የሚያሳርፍ ለቅሶውን ደግሞ በደስታ
አዝማች · Chorus
አቤት አቤት ኢየሱሴ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት)
ቁጥር 7 · Verse 7
አቤት አቤት አባባ እንደአንተ ያለ
እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ
ቁጥር 8 · Verse 8
ቸርነትህን ምህረትህን በሕይወቴ አይቻለሁ
ራራህልኝ የእኔ ጌታ ያለፈውን ረስቻለሁ
ስብራቴን ጠግነኸው ቀና አድርገህ አራመድከኝ
ቁሻሻዬን አስወግደህ ንጹህ ልቤስን አለበስከኝ
አንተው ብቻ ግነህልኝ የእኔ ኢየሱስ ግነህልኝ
ዛሬም አንተው ነህ መኩራዬ የዘለዓለም ማረፊያዬ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና
ለጌታ ለአምላኬ ይገባዋልና
ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና
ለጌታ ለአባቴ ይገባዋልና
ቁጥር 9 · Verse 9
ኢየሱሴ የእኔ ጌታ ጉልበቴ ነህ እወድሃለሁ
አንተ አለቴ መድሃኒቴ አምባዬ ነህ አመልክሃለሁ
ስትረዳኝ ስታግዘኝ ስታጽናናኝ አየሁ በዐይኔ
ምን እላለሁ ማዳንህን አወራለሁ በዘመኔ
አንተው ብቻ ግነህልኝ??? የእኔ ኢየሱስ ግነህልኝ
ዛሬም አንተው ነህ መኩራዬ የዘለዓለም ማረፊያዬ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና
ለጌታ ለአምላኬ ይገባዋልና
ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና
ለጌታ ለአባቴ ይገባዋልና
ቁጥር 10 · Verse 10
ብርና ወርቅ አልማዝ ዕንቁ ቀይም ዘምቤል አያክል
ለእኔ እኮ አንተ ከዚም በላይ
ታበራለህ ውብ እኮ ነህ
ደም ግባቴ ዛሬም ጥርሴ
ሞገሴ ነህ የእኔ ጌታ
ላመስግንህ በዝማሬ በሆታና በዕልልታ
አንተው ብቻ ግነህልኝ የእኔ ኢየሱስ ግነህልኝ
ዛሬም አንተው ነህ መኩራዬ የዘለዓለም ማረፊያዬ ሃሌሉያ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና
ለጌታ ለአምላኬ ይገባዋልና
ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና
ለጌታ ለአባቴ ይገባዋልና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ