Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አባቴ

Abatie

6:14 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

መልካም ነህ ለእኔ አባቴ (፪x)

ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ

ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ (፪x)

ይሁንልኝ ብዬ የተሟገትኳቸው

ባለፈው ዘመኔ ኧረ ብዙ ናቸው

ጊዜ ፈጀሁ እንጂ ከወዲህ ከወዲያ

ምን ጥልቅ አስብሎኝ ደርሶ በአንተ ሞያ

ትክክል ነህ ጌታ በሥራህ ጻድቅ ነህ

አንተ አትታረምም እንዲህ አድርግ ተብለህ

መልካም ነህ ለእኔ አባቴ (፪x)

ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ

ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ (፪x)

እንደው መጨነቄ ሁሉ ከልኩ አያልፍ

አንዳችም ላልጨምር አንዳችም ላላተርፍ

ባይገቡኝም እንኳን መንገዶቼ ሁሉ

ለአንተ ግን አባቴ ጠርተው ይታያሉ

ለእኔ የምታስበው መልካም ከሆነልኝ

እንዳረከኝ ልሁን የእኔስ ይቅርብኝ

እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም

አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ

ስኖር በዚች ዓለም

አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ

ስኖር በዚች ዓለም (፪x)

እግሮቼን ከወጥመድ ማነው ያወጣቸው

ዓይኖቼ ሁልጊዜ ጌታ ወደ አንተ ናቸው

በመረጥከው መንገድ አስተምረኸኛል

ለማያልፈው ሕይወት መኖር ይሻለኛል

ለማያልፈው መብል መስራት ይሻለኛል

መልካም ነህ ለእኔ አባቴ (፪x)

ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ

ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ (፪x)

እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም

አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ

ስኖር በዚች ዓለም

አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ

ስኖር በዚች ዓለም (፪x)

ትክክል ነህ ጌታ በሥራህ ጻድቅ ነህ

አንተ አትታረምም እንዲህ አድርግ ተብለህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ