አምላኬ
Amlakie
4:52 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሃፍረት አስቀርቅሮ አንገቴ ላይ ቀና
የበደሌ ቀንበር በላዬ ባሰና
በቀራንዮ ላይ ባፈሰስከው ደምህ
ድፍረት ሆኖልኛል እንድቆም በፊትህ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x)
ክብሬ ነህ ማዕረጌ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሥምህን ጠርቼ ድኛለሁኝና (አምላኬ)
በላይ በላዩ ላይ ልደርብ ምሥጋና (አምላኬ)
ኧረ እኔ አመለጥኩኝ አንተን በማመኔ (አምላኬ)
በሰውነቴ ላይ ታወቀኝ መዳኔ (አምላኬ)
ታድያ እንዴት ዝም ይላል የተደረገለት (አምላኬ)
በድግድግ ጨለማ ብርሃን የሆንክለት (አምላኬ)
አዝማች · Chorus
አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x)
ክብሬ ነህ ማዕረጌ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተን በመምረጤ አላፈርኩም ከቶ
ሰላም ሆኖልኛል ቃልህ ልቤ ገብቶ
መታመኛዬ ነህ ኮርቼብሃለሁ
በሕይወቴ ዘምን አንተን አመልካለሁ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x)
ክብሬ ነህ ማዕረጌ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ስገጅ ስገጅ አለኝ ተገርፈሃልና (አምላኬ)
ልሰጥ የሚገባኝ ይኸው የእጅ መንሻ (አምላኬ)
ግሩም የዕርቅ ቀን ስለሆነ ለእኔ (አምላኬ)
ምሥጋናዬ ኢኸው ይፈሳል ከልቤ (አምላኬ)
ከጻድቃን ማህበር እኔም ልቀላቀል (አምላኬ)
ለዚህ በቅቻለሁ ለክብር ልታሰብ (አምላኬ)
ቁጥር 5 · Verse 5
አምላኬ (አምላኬ) ፣ አምላኬ (አምላኬ) (፫x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ክብሬ ነህ ማዕረጌ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ