ታሪክ
Tarik
4:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው አነሰ አይባል እከሌ ነኝ ይላል
ከስሙ አስቀድሞ ያለ የሌለ ነገር ጨማምሮ ይናገራል
ሥራህስ ምንድን ነው ብለው ቢጠይቁት
አሳምሮ ያወራል ያብራራል ከሰሙት
ለመጥምቁ ዮሐንስ ኢሄ እድል ደረሰው
አንተ ማነህ ብሎ ብዙ ህዝብ ጠየቀው
እንዲህ ሲል መለሰ ስለ ማንነቱ
ሳያፍር ገለጠ እውነትን ከውሸቱ
እኔ ጠራጊ ነኝ ፣ ድምጽ ነኝ ፣ ምጮኸው
መንገድ የማዘጋጅ ከኋላ ሄዳለሁ
አይደለሁም ኤልያስ ከነብያቶች አንዱ
የማመቻች ነኝ ጥርጊያ ለመንገዱ
አላቸው መልሶ ራሱን አሳንሶ
የጫማውን ጥፍር ልፈታ የማይገባኝ
ከእርሱ አንሳለሁኝ
እኔ ላንስ ይገባል እርሱ ከእኔ ይበልጣል
እኔ በውኃ ሳጠምቅ በእሳት ያጠምቃል
እርሱ ከእኔ ይበልጣል[1][2]
አዝማች · Chorus
እንዲህ ነው እንግዲህ ትህትና
እንዲህ ነው እንግዲህ ዝቅ ማለት (፪x)
ራስን ማወቅ ማንነትን
ሰው መሆንን መረዳትን
ያበዛዋል መዋረድን
ሒሳቡ ደግሞ ኢሄ ነው
ዝቅ ያለ ነው ከፍ የሚለው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔ (፮x) ባልኩኝ ቁጥር
እወጣለሁኝ ካለሁበት አጥር
እኔ (፮x) ያልኩኝ ለታ
ያበቃልኛል የማታ የማታ
እኔነቴ መድከሚያዬ
እኔነቴ መውደቂያዬ
እኔነቴ መወጫዬ
እኔነቴ መቃብሬ
ስንቱ ተቀበረ በእኔነት መቃብር
ትንሳዔ ያምጣለት ትሁቱ እግዚአብሔር (፪x)
እንደ እንጀራ አይለመን ትህትና
መለወጥ ነዉ ፣ መወሰን ነዉ ፣ የሚያስፈልገዉ
በትዕቢት ከጋሉ
አዝማች · Chorus
እኔነቴ መድከሚያዬ
እኔነቴ መውደቂያዬ
እኔነቴ መወጫዬ
እኔነቴ መቃብሬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ