የእኔ ምስጋና
Yenie Mesgana
4:51 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የእኔ ምሥጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውኃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የእኔ ምሥጋና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ወይ ዘንቦ ላይዘንብ ወይ ጥሎ ላይጥል
መብረቁ ሲያስፈራ ሲል ብልጭ ድርግም (፪×)
ነጐድጓዱ ታሞ ጠብ እንኳን ካላለ
ዝናብ ፈርቶ ሰው ቤቱ ከዋለ ተታለለ
ግርግር ባይኖር ሙዚቃ ባልሰማ
የነፍሴ ምሥጋና ዙፋኑ ይሰማ
አዝማች · Chorus
ዝናብ እንደሌለው ደመና
አይደለም የእኔ ምሥጋና
ቁጥር 2 · Verse 2
የእኔ ምሥጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውኃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የእኔ ምሥጋና
ቁጥር 3 · Verse 3
እህሉ ሊበላሽ ዘንቦበት በረዶ
እያለ ሲያወራ ካሁን አሁን ወርዶ በረዶ
ጉሙ ሲያጉረጐርም መጣሁኝ እያለ
ደመናው ሰንጥቆት ፀሐይ ብቅ ካለ ተታለለ
ዝም ብዬ የምጮህ እንዲያው ባዶ ሜዳ
አይደለሁም እኔስ ሞልቶኛል ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ዝናብ እንደሌለው ደመና
አይደለም የእኔ ምሥጋና
ቁጥር 4 · Verse 4
ምሥጋና ምሥጋና (፪x)
እሰዋለሁ ለጌታዬ ለአምላኬ
ይገባዋልና በከፍታ በዝቅታ
አምልኮዬን አቀርባለሁ ለእርሱ ክብር በደስታ
ምሥጋና ምሥጋና (፪x)
ለጌታዬ ለታደገኝ ለአዳነኝ
ለክብሩ ዝቅ እያልኩኝ እየሰገድኩ እያመለኩ
ፊቱ ብወድቅ ባደንቀው ባሞግሰው ለእርሱ አይበቃም
አዝማች · Chorus
የእኔ ምሥጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውኃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የእኔ ምሥጋና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ