Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ታሪኬ የጀመረው

Tarikie Yejemerew

6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ታሪኬ የጀመረው (፫x)

በመስቀሉ ሥር ነው (፪x)

የተነሳበትን የማያውቅ

የሚደርስበትን አያውቅም

የተወለድኩ ቀን ታሪኬ

እንደተጀመረ እንኳን ባላወቅም

ከዚህ ዕውቀት ልኩ ያለፈ

ሌላ ዕውቀት ተገልጦልኛል

የታሪኬ ጅምር መነሻው

ከመስቀሉ ግርጌ ሆኖኛል

ያወኩት ቀን አምላኬን ጌታዬ

ስቀበለው እንደግል አዳኜ

ስመዘገብ በሕይወት መዝገብ ላይ

ጀማመረ ታሪኬ እዚያ ላይ (፪x)

ታሪኬ የጀመረው (፫x)

በመስቀሉ ሥር ነው (፪x)

ሰው ሞቶ ሲሸኝ ወደ ቀብር

ሁሉም አልቅሶ ይሸኘዋል

ቀብረው ሲመለሱ ታሪኩን

በቃ ሁሉም ይዘነጉታል

የእኔ ግን ከዚህ የተለየ ነው

ታሪኬ እዛ ላይ አያበቃም

ወደ ዘለዓለማዊው ሃገሬ

ጭራሽ ወደ ሌላ ይሻገራል

ነፍሴ ከሥጋዬ ስትለያይ

ወደ ጌታዋ ስትሄድ ወደ ላይ

ሌላ ታሪክ ደግሞ ጀምራለሁ

ወደ አዳነኝ ጌታ እሄዳለሁ (፪x)

ታሪኬ የሚቀጥለው (፫x)

ከሞት ባሻገር ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ