ይገባ ነበር ዎይ
Yigeba Neber Woy
4:45 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኤሎሄ ኤሎሄ
ላማ ሰበቅታኒ [1][2]
ይገባ ነበር ዎይ ስለ እኔ ማልቀስህ
ይገባ ነበር ዎይ እንዲያ መዋተትህ
ይገባ ነበር ዎይ መስቀል ላይ መሞትህ
ዎይ (፲፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ይዘዉህ ሲሄዱ እንደሚታረድ በግ
ዝም ብለህ እየሄድክ አንዳች ሳትሟገት
ማነኝ ለመሆኑ እንዴት እወደድከኝ
ከክብር ላይ ወርደህ የተዋረድክልኝ
አቤቱ ፍቅርህ ጥልቀቱ
አቤቱ መውደድህ ስፋቱ
አይመረመርም በሰው ዘንድ
ታላቅ ነው ጌታ የአንተ መውደድ
ፊቴ ድቅን ይላል የእሾህ ጉንጉኑ
የጅራፉ ብዛት የገላ ሰንበሩ
አዝማች · Chorus
ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ [1][2]
ብለህ ስትጨነቅ ስለእኔ ስትማቅቅ
አቤቱ ፍቅርህ ጥልቀቱ
አቤቱ መውደድህ ስፋቱ
አይመረመርም በሰው ዘንድ
ታላቅ ነው ጌታ የአንተ መውደድ
ቁጥር 2 · Verse 2
ይገባ ነበር ዎይ ጻድቅ አይደለህ ዎይ
ይገባ ነበር ዎይ ንጹህ አይደለህ ዎይ
ጻድቅ ሰው በመስቀል እርቃኑን አደረ
ስለ ኃጥያተኞች ደሙን አፈሰሰ
ይገባ ነበር ዎይ ስለ እኔ ማልቀስህ
ይገባ ነበር ዎይ እንዲያ መዋተትህ
ይገባ ነበር ዎይ መስቀል ላይ መሞትህ
ዎይ (፲፫x)
አዝማች · Chorus
አቤቱ ፍቅርህ ጥልቀቱ
አቤቱ መውደድህ ስፋቱ
አይመረመርም በሰው ዘንድ
ታላቅ ነው ጌታ የአንተ መውደድ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ