አንሰዋም
Anasewam
4:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሆ (፰x)
ህዝቡን ከባርነት ፈልቅቆ ያወጣ
ከድንጋይ ላይ ውኃን አፍልቆ ያጠጣ
በመሪባ ውኃ ያረሰረሳቸው
በሲና ተራራ ያነጋገራቸው
አምላካችን እርሱ ሥሙም እግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔርን እንወደዋለን (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሙዚቃውን ስትሰሙ ለቆመው ለምስጉን
ለአምላኬ ወድቃችሁ ስገዱ ሲባሉ
እንኳንስ ሊሰግዱ ቢንቀለቀል ቶኑ
ፈፁም ፍንክች አይሉም ሶስቱም ከጨከኑ
ከአምላካቸው ሌላ ለማንም አይሰግዱ [1]
ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ አናውቅም
ከእርሱ በቀር ሌላ አናመልክም
ለአምላካችን እንሰግድለታለን
ለእግዚአብሔር እንሰዋለታለን
አንሰዋም ለባዳን አማልክት
አንሰግድም ለሠማይ ሠራዊት
ስግደትን ስግደት ለሚገባው
ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ገና ያኔ ገና ሠማይ ምድርን ሲሰራ (ኡ ኦ ኡ ኦ)
ቀላያትን ሲቀድ ብርሃንን ሲያበራ (ኡ ኦ ኡ ኦ)
ይሁን ያለው ሁሉ ሁሉ ለሆነለት
ክብር ይሁን ክብር ለፍጥረታት አባት
ለአምላካችን ለእርሱ ለፈጠረን ጌታ
ዘለዓለም ይድረሰው ክብርም ምሥጋና (፪x)
አዝማች · Chorus
ሆ ብለን እንሄዳለን እናመልከዋለን
ሆ ብለን እንሄዳለን እንሰግድለታለን (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንሰዋም ለባዳን አማልክት
አንሰግድም ለሠማይ ሠራዊት
ስግደትን ስግደት ለሚገባው
ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ሆ ብለን እንሄዳለን እናመልከዋለን
ሆ ብለን እንሄዳለን እንሰግድለታለን (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ