Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንዲህ አይደረግም

Endih Ayderegem

4:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የእኔን ሰው መሆን የፍጥረቴን ሚስጥር

የደመነፍስ:ኑሮን ጠፍቶ የሚተረትር

የታረደለኝ በግ ትርጉም ያለው ሕይወት ፣ ያለኝ ነኝ

እኔም ዝቅ በዬ ልስገድለት ለእርሱ

ምሥጋና ነው ያለኝ

ምሥጋና (፬x) ነው ያለኝ (፪x)

ተከተይኝ አለኝ ትምክቴን አስጥሎ

የዓለም አይደለሽም አንቺ የእኔ ነሽ በሎ

አክብሮት አምልኮ ለሌላው ለመስጠት

ጉልበቶቼ ታጥፈው ሊንቀጠቀጡለት

እንዲህ አይደረግም (፪x)

ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም (፪x)

ያልሳሳ ገበታን ጌታዬ አዘጋጅቶ

ከሕይወት ቃል ማዕድ መንፈሴን አርክቶ

እንዳዜም ካበቃኝ በሕያዋን ምድር

ልሰግድ ይገባኛል ከንጉሡ እግር ሥር

ይገባኛል (፪x)

አምላኬ እኮ እኔን ሌላ ሰው አርጐኛል (፪x)

ከምድራዊው ኑሮ ያለፈ አለ ብሎ

የሞተልኝ ጌታ የእኔን እዳ ከፍሎ

ክርስቶስን ለበስኩ እንዴት አምሮብኛል

ክብሬና ሞገሴን ማን ያወልቅብኛል

እንዲህ አይደረግም (፪x)

ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም (፪x)

የእኔን ሰው መሆን የፍጥረቴን ሚስጥር

የደመነፍስ:ኑሮን ጠፍቶ የሚተረትር

የታረደለኝ በግ ትርጉም ያለው ሕይወት ፣ ያለኝ ነኝ

እኔም ዝቅ በዬ ልስገድለት ለእርሱ

ምሥጋና ነው ያለኝ

ምሥጋና (፬x) ነው ያለኝ

ዕልልታ (፬x) ነው ያለኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ