Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አበርታኝ

Abertagn

2008 · ትራክ 11 · 5:40 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያልከው ይሆናል (፫x)

አንተ ያልከው ይሆናል (፪x)

ከአፍህ ቃል ወጥቶ አንተ ተናግረህ

ተስፋ ያረገ አንተን መቼ ከሰረ

ሆኖለት ሁሉ ተደላድሎብህ

ስጋቱ ጠፋ እፎይ ብሎብህ (፪x)

እንደ ሰው አይደል መች ትዋሻለህ

ያልከው ይሆናል ትፈጽማለህ

አምረህ ውብ ሆነህ አንተ ያልከው

ጌታ የተናገርከው ሁሉን አሳመርከው (፪x)

ያልከው ይሆናል (፫x)

አንተ ያልከው ይሆናል (፪x)

ከአፍህ ቃል ወጥቶ አንተ ተናግረህ

ተስፋ ያረገ አንተን መቼ ከሰረ

ሆኖለት ሁሉ ተደላድሎብህ

ስጋቱ ጠፋ እፎይ ብሎብህ (፪x)

የአንተ ቃል ቃል ነው አይታጠፍም

እንዲሁ መጥቶ አይመለስም

ይሰራል ያደርጋል ይለውጣል

ቃል አጽንቶ ያቆማል ዛሬም ሕያው ሆኗል (፪x)

ያልከው ይሆናል (፫x)

አንተ ያልከው ይሆናል (፪x)

ከአፍህ ቃል ወጥቶ አንተ ተናግረህ

ተስፋ ያረገ አንተን መቼ ከሰረ

ሆኖለት ሁሉ ተደላድሎብህ

ስጋቱ ጠፋ እፎይ ብሎብህ (፪x)

አየሁህ ዛሬ ስትሰራ በእኔ

ቃልህን ፈጸምከው ታማኝ ነህ ለእኔ

ወጣሁኝ አቆመኝ እንደገና

ላሰማ ምሥጋና ድንቅ አድርጓልና (፪x)

ያልከው ይሆናል (፫x)

አንተ ያልከው ይሆናል (፪x)

ከአፍህ ቃል ወጥቶ አንተ ተናግረህ

ተስፋ ያደረገ አንተን መቼ ከሰረ

ሆኖለት ሁሉ ተደላድሎብህ

ስጋቱ ጠፋ እፎይ ብሎብህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ