እፎይ
Efoy
2008 · ትራክ 6 · 5:36 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የግሌ ነህ ወዳጄ (፫x)
የእራሴ ነህ ወዳጄ (፫x)
ወዳጅ የሚሏቸው አንድ ቀን ሲለዩ
የቅርቤ ያልኳቸው ከአንተ ሰስተያዩ
ግን አንተ ጥለህ የማትሄድ
የማትከዳ አብዝተህ የምትወድ
ወዳጄ ብዬ የማላፍርብህ
አንተን ነው የእራሴ ያረኩህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የእራሴ አልኩኝ ጉያህ ሥር ሆኜ
አንዳች ላይነካኝ በአንተ ታምኜ
የግሌን ወዳጅ ማን ሊወስድብኝ
ሌላውን ትቼ ስሩ ገባሁኝ
የእራሴ አልኩኝ
የእራሴ የእራሴ የእራሴ
የግሌ የግሌ የግሌ
አዝማች · Chorus
የግሌ ነህ ወዳጄ (፫x)
የእራሴ ነህ ወዳጄ (፫x)
ወዳጅ የሚሏቸው አንድ ቀን ሲለዩ
የቅርቤ ያልኳቸው ከአንተ ሰስተያዩ
ግን አንተ ጥለህ የማትሄድ
የማትከዳ አብዝተህ የምትወድ
ወዳጄ ብዬ የማላፍርብህ
አንተን ነው የእራሴ ያረኩህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከእንግዲህ አልፈራም ምን እሆን ብዬ
የያዝኩት ታማኝ ሆኖኝ ጋሻዬ
ጥሎኝ አልሄድም መንገድ ላይ ትቶ
ና ልጄ እያለ እጄን ጐትቶ
አስገባኝ ቀቶ
አስገባኝ አስገባኝ አስገባኝ
አስጠጋኝ አስጠጋኝ አስጠጋኝ
ተደላደልኩኝ ወዳጅ አገኘሁ
እፎይ የሚያስብል የሚመች ነው
ጊዜ አይቶ አይርቅም ሁልጌዜ ያው ነው
ስጋት አይገባኝ ልቤ ሙሉ ነው
እፎይ ብያለሁ
እፎዪ እፎዪ እፎዪ እፎይ (፪x)
አዝማች · Chorus
የግሌ ነህ ወዳጄ (፫x)
የእራሴ ነህ ወዳጄ (፫x)
ወዳጅ የሚሏቸው አንድ ቀን ሲለዩ
የቅርቤ ያልኳቸው ከአንተ ሰስተያዩ
ግን አንተ ጥለህ የማትሄድ
የማትከዳ አብዝተህ የምትወድ
ወዳጄ ብዬ የማላፍርብህ
አንተን ነው የእራሴ ያረኩህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ