Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በጨነቀኝ ጊዜ

Becheneqegn Gizie

2008 · ትራክ 5 · 4:31 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በጨነቀኝ ጊዜ ፀሎቴ

በእንባ ስነግርህ ጭንቀቴን

ለካስ ሰምተኸኛል ተመሥገን

ነዶ አስታቀፍከኝ ያማረውን

በዚያ በጣር ጊዜ ለሰማኸኝ

በሄድኩበት ሁሉ ለመራኸኝ

ይሰዋ በፊትህ ምሥጋናዬ

ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (፪x)

ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (፬x)

ሁሉ አልፎ ዛሬ ዘምራለሁ

የቃርሚያውን ሕይወት አልፌያለሁ

እልፍ አደረገኝ አከበረኝ

በአምላኬ ከፍታን አገኘሁኝ

በዚያ በጣር ጊዜ ለሰማኸኝ

በሄድኩበት ሁሉ ለመራኸኝ

ይሰዋ በፊትህ ምሥጋናዬ

ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (፪x)

እንደመሸ አልቀረም ነግቶልኛል

ከአምላኬ ጉብኝት ሆኖልኛል

የጨለማው ዘመን አለፈና

ልዘምር በቃሁኝ አልኩኝ ቀና

በዚያ በጣር ጊዜ ለሰማኸኝ

በሄድኩበት ሁሉ ለመራኸኝ

ይሰዋ በፊትህ ምሥጋናዬ

ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ