Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተስፋ አለኝ

Tesfa Alegn

2008 · ትራክ 3 · 4:46 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እኔስ ተስፋ አለኝ (፬x)

የተገባልኝ የተስፋ ቃል አለኝ

ተስፋዬም አንድነው ተስፋን የሰጠኝ (፪x)

የገባልኝን ቃሉ ይፈጽማልና

ይዋሽ ዘንድ ጌታ ሰው አይደለምና

እውነት ተናጋሪ ያለውን የሚፈጽም

ቃልኪዳን አክባሪ እንደ እርሱ ያለ የለም

ቃልኪዳን አክባሪ እንደ እርሱ ያለ የለም (፬x)

እኔስ ተስፋ አለኝ (፬x)

የተገባልኝ የተስፋ ቃል አለኝ

ተስፋዬም: አንድነው ተስፋን የሰጠኝ (፪x)

እኔ የምመካበት የምታመንበት

ተስፋዬ ነው ብዬ የምደገፍበት

አለኝ አለኝ የምለው ተስፋን የሰጠኝ

ተስፋዬ እግዚአብሔር ነው ሌላው አይሆነኝም

ተስፋዬ እግዚአብሔር ነው ሌላው አይሆነኝም (፬x)

እኔስ ተስፋ አለኝ (፬x)

የተገባልኝ የተስፋ ቃል አለኝ

ተስፋዬም አንድነው ተስፋን የሰጠኝ (፪x)

ተስፋ እንደሌለው ሰው ተስፋዬን አልቆርጥም

ብዙ ተስፋ አለው መድሃኒያዓለም

ያየልኝ ብዙ አለ ለእኔ የተመኘው

ታዲያለሁ በቃ ተስፋዬ እግዚአብሔር ነው

ታዲያለሁ በቃ ተስፋዬ እግዚአብሔር ነው (፬x)

እኔስ ተስፋ አለኝ (፬x)

የተገባልኝ የተስፋ ቃል አለኝ

ተስፋዬም: አንድነው ተስፋን የሰጠኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ