Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዘምር አለኝ

Zemer Alegn

2008 · ትራክ 10 · 5:15 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዘምር አለኝ (፬x)

ሥራህ ተሰርቷል ዘምር

ቀንበር ተሰብሯል ዘምር

ማልቀስ አበቃ ዘምር

እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ዘምር (፪x)

አለኝ

የሚያስለቅስህን በእኔ ላይ ጣለው ብሎኛል (፪x)

እርሱ እያለ ለምን ልሥጋ

ጌታ እኮ ነው ከእኔ ጋራ

የማምለጫ ዓለቴ ነው

ጋሻዬና ምርኩዜም ነው (፪x)

ዘምር አለኝ (፬x)

ሥራህ ተሰርቷል ዘምር

ቀንበር ተሰብሯል ዘምር

ማልቀስ አበቃ ዘምር

እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ዘምር (፪x)

አለኝ

እኔ ከአንተ ጋር ነኝ አትስጋ ብሎኛል እርሱ (፪x)

አልደነግጥ ከቶ አልፈራ

ባለ ድል ነኝ ከአምላክ ጋራ

ጠላቶቼ ሰምጠው ቀሩ

አሻገረኝ ኢኸው ለክብሩ (፪x)

ዘምር አለኝ (፬x)

ሥራህ ተሰርቷል ዘምር

ቀንበር ተሰብሯል ዘምር

ማልቀስ አበቃ ዘምር

እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ዘምር (፪x)

አለኝ

ሁሌ ደስ ይበልህ በእኔ ደስ ይበልህ አለኝ፪

መቆዘሜ ለምንድን ነው

መተከዜስ ለምንድን ነው

ለሚያልፈው ለዚህ ምድር

መዘመር ነው ለእርሱ ክብር (፪x)

ዘምር አለኝ (፬x)

ሥራህ ተሰርቷል ዘምር

ቀንበር ተሰብሯል ዘምር

ማልቀስ አበቃ ዘምር

እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ዘምር (፪x)

አለኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ