ለየት አድርጐልኛል
Leyet Adergolegnal
2008 · ትራክ 12 · 4:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የአምላኬ ስራው ይገርመኛል
የኢየሱሴ ስራው ይደንቀኛል (፪x)
ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ሠማይን
ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ምድርን
አዝማች · Chorus
ይገርማል (፫x)
ሥራው ያስገርማል
ይደንቃል (ይደንቃል) (፫x)
ሥራው ያስደንቃል
ቁጥር 2 · Verse 2
ይሁን ብሎ ከፈጠራቸው
በቃል ብቻ እርሱ ካደረጋቸው
እኔን ለየት አድርጐኛል
ጌታዬ በአምሳሉ ፈጥሮኛሉ (፪x)
ይሁን ብሎ ከፈጠራቸው
በቃል ብቻ እርሱ ካዘዛቸው
እኔን ለየት አድርጐኛል
ጌታዬ በአምሳሉ ፈጥሮኛሉ (፪x)
ፍጥረትን ሲፈጥር የሚገርመኝ ለእኔ
ሠማይ ይሁን አለ ሁነ ድሮ ያኔ
ይሁን ከተባለው ለየት አድር
እርሱን የምመስል ውብ አድርጐ ሰርቶኛል
ገዢ አደረገኝ በፍጥረት ሁሉ ላይ
የበላይ እንድሆን ትዛዝ ሰጠኝ ከላይ
ልዩ ሰው አድርጐ በምድር አስቀመጠኝ
ይሁን ብሎ ሳይሆን በእጆቹ ሰራኝ
አዝማች · Chorus
ይገርማል (፫x)
ሥራው ያስገርማል
ይደንቃል (ይደንቃል) (፫x)
ሥራው ያስደንቃል
ቁጥር 3 · Verse 3
የአምላኬ ስራው እኔስ ይደንቀኛል
ከአፉ የሚወጣው ቃል አስገርሞኛል
ቃል ተናግሮ ብቻ ሁሉን ውብ አረገ
እኔን በእራሱ አምሳል ቀርጾኝ
ለየት አደረገ
የአምላኬ ስራው ይገርመኛል
የኢየሱሴ ስራው ይደንቀኛል (፪x)
ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ሠማይን
ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ምድርን
አዝማች · Chorus
ይገርማል (፫x)
ሥራው ያስገርማል
ይደንቃል (ይደንቃል) (፫x)
ሥራው ያስደንቃል
ቁጥር 4 · Verse 4
ይሁን ብሎ ከፈጠራቸው
በቃል ብቻ እርሱ ካዘዛቸው
እኔን ለየት አድርጐኛል
ጌታዬ በአምሳሉ ፈጥሮኛሉ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ