አንደኛ
Andegna
2008 · ትራክ 8 · 5:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም
ሊዘራ ሲነሳ አንዳች አያግደውም
ባለ ብዙ ግርማ አሃ
ባለ ብዙ ዝና አሃ
እንደ አንተ ያለ ጌታ
ኃይልህ የበረታ
ሁሌ ድል ነሺ ነህ
አንተን ማን ሊረታህ
አዝማች · Chorus
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ (፬x)
አንተን ማን ሊረታህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታዬ ስትሰራ የሚያግድህ የለ
አማካሪ ሳይኖር ሁሉን ታደርጋለህ
በኃይል በችሎትህ አንተ የበረታህ
አቅምህ ሙሉ ነህ መቼም አትረታ
ድል ነሽ አንደኛ አንተ የሁሉ ዳኛ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም
ሊዘራ ሲነሳ አንዳች አያግደውም
ባለ ብዙ ግርማ አሃ
ባለ ብዙ ዝና አሃ
እንደ አንተ ያለ ጌታ
ኃይልህ የበረታ
ሁሌ ድል ነሺ ነህ
አንተን ማን ሊረታህ
አዝማች · Chorus
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ (፬x)
አንተን ማን ሊረታህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የሠማይ አንደኛ የምድር አንደኛ
ኢየሱስ አንተ ነህ በዓለም ላይ ብቸኛ (፪x)
በእኔ ልትጠቀም በእኔ ልትሰራ
ነጥቀህ አወጣኸኝ ከዚያ ባለጋራ
አዲስ ጉዞ ጀመርኩ ከእርሱ ጋር ወደፊት
ትንሳኤ ሆነልኝ ሞቴ ወደ ሕይወት
ገረመኝ መዳኔ እኔ የአንተ መሆኔ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም
ሊዘራ ሲነሳ አንዳች አያግደውም
ባለ ብዙ ግርማ አሃ
ባለ ብዙ ዝና አሃ
እንደ አንተ ያለ ጌታ
ኃይልህ የበረታ
ሁሌ ድል ነሺ ነህ
አንተን ማን ሊረታህ
አዝማች · Chorus
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ (፬x)
አንተን ማን ሊረታህ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ካልታሰበ ስፍራ ከተናቀ ቦታ
ታናሹ ሊከብር ሊታሰብ በጌታ
ኮተቱን ሊያስጥለው ወደላይ ሊያወጣው
ተራው ደረሰለት ከፍታው ላይ ሊያወርሰው
ከበረ ትንሹ ፈጣን ነው ደራሹ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም
ሊዘራ ሲነሳ አንዳች አያግደውም
ባለ ብዙ ግርማ አሃ
ባለ ብዙ ዝና አሃ
እንደ አንተ ያለ ጌታ
ኃይልህ የበረታ
ሁሌ ድል ነሺ ነህ
አንተን ማን ሊረታህ
አዝማች · Chorus
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ
አንደኛ ነህ ጌታ አንደኛ (፬x)
አንተን ማን ሊረታህ (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
የሠማይ አንደኛ የምድር አንደኛ
ኢየሱስ አንተ ነህ በዓለም ላይ ብቸኛ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ