Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አድነነ

Adenene

2011 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የእውነት መልክ ያለው ከእውነት የተጣላ

የጊዜውን ያየ የነገው ተላላ

በሌላው ላይ ፈራጅ ጣቶቹን ቀሳሪ

ስለእራሱ ኑሮ ሕያውን ቀባሪ

ካባው የሸፈነው መቃብርነቱን

የምላሱ ቂቤ አጥምዶ አረካለት

የልብ አውሬነቱን

አድኅነነ ከመዐቱ ሰውረነ ፣

ስማነ አምላክነ ወመድኃኒነ (፪x)

(ይቅርብኝ) ላይጠቅመኝ ይቅርብኝ

(ይቅርብኝ) ቢቀርብኝ ሞት ነው

(ይቅርብኝ) ለካ የተወዳጀኝ

(ይቅርብኝ) ተንቀሳቃሽ ሞት ነው

(ይቅርብኝ) የፍቅር ሰው መሳይ

(ይቅርብኝ) የወንድም አታላይ

(ይቅርብኝ) ስንቱን ወጥቶ ጣለው

(ይቅርብኝ) ያልብሾት ተናኝ

ታረቅ ከራስህ ጋር ወገኔ

ሁሉ ያመልጥሃል ስትል ለእኔ ፣

መኖር ልመድ እንጂ ለሌላዉ

ያ ነው የሕይወት ተድላ ደስታዉ (፪x)

አድኅነነ ከመዐቱ ሰውረነ ፣

ስማነ አምላክነ ወመድኃኒነ (፪x)

ጣኦት ተሰይፎ መቅደሽን ይዘርፋል

ሕሊናህን ጥሶት አካልህ ይሮጣል

ልጓም አበጂለት ራስህ ከአንተ ወጥቷል

ሁለት ሰው ሆነህ መታወቂያህ ጠፍቷል

ሩቅ አሳቢ ሆነህ በቅርቡ አዳሪ

የአፍ ብቻ አርበኛ አስጐምጅቶ በላ

አንቱ ፈሪሳዊ

እኔነቴን ፥ በእኔው ያለ የእኔው ጠላቴ ፣

አላወጣው ውስጤ በእኔው ነዋሪ ቤቴ

ኖሮ እንዳያጠፋኝ ንቃልኝ ውስጠቴን (፪x)

ማረን ማረን ይቅር በለን

ስማን ስማን ተቀበለን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ