ተወራርጃለሁ
Tewerarejalehu
2011 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተወራርጃለሁ እኔማ ያወጣኛል ብዬ
ተወራርጃለሁ እኔማ እርሱ አለልኝ ብዬ
ተወራርጃለሁ እኔማ የኢየሱስ ነኝ ብዬ
ተወራርጃለሁ እኔማ አይጥለኝም ብዬ
አይጥልማ (አይጥልማ) አይረሳማ (አይረሳማ) (፪x)
ይታመናል እግዚአብሔር አይጥልማ
ይታመናል እግዚአብሔር አይረሳማ (፬x)
የይለፍ ቃል አለኝ ተሻገር ብሎኛል
ፋሬስ ብዬ ልውጣ ጌታ ቀድሞልኛል
የኋላዬን ሁሉ የኋሊት ረስቼ
ልገስግስ በእምነት ጌታን ተመኝቼ
ልሻገር በእምነት እርሱን ተመክቼ
ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይይታመናል ኢየሱስ ይታመናል
ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይታመናል እርሱ ይታመናል (፫x)
ገና ለአንተ ክብር (ለአንተ ክብር)
ገና ለአንተ ዝና (ለአንተ ዝና)
ገና እዘምራለሁ (እዘምራለሁ)
ገና እንደገና (፪x)
ለእግዚአብሔር እኔማ ለእግዚአብሔር
አለኝ ብዙ ምሥጋና ብዙ ክብር
ለኢየሱሴ እኔማ ለኢየሱሴ
አለኝ ብዙ ምሥጋና ብዙ ውዳሴ
አለኝ አለኝ ምሥጋና ለአዳነኝ
ከእጆቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ መጣ
ጠላቴ መሸበት ለእኔ ሌቱ ነጋ
የተናገረኝን እስከሚፈጽመው
አይጥለኝም አለ እግዚአብሔር ታማኝ ነው
አይተወኝም አለ እግዚአብሔር ታማኝ ነው
ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይይታመናል ኢየሱስ ይታመናል
ይታመናል ጌታ ይታመናል
ይታመናል እርሱ ይታመናል (፫x)
አዝማች · Chorus
ተወራርጃለሁ እኔማ ያወጣኛል ብዬ
ተወራርጃለሁ እኔማ እርሱ አለልኝ ብዬ
ተወራርጃለሁ እኔማ የኢየሱስ ነኝ ብዬ
ተወራርጃለሁ እኔማ አይጥለኝም ብዬ
አይጥልማ (አይጥልማ) አይረሳማ (አይረሳማ) (፪x)
ይታመናል እግዚአብሔር አይጥልማ
ይታመናል እግዚአብሔር አይረሳማ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ