ሌሊቱ ነጋ
Lielitu Nega
2011 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ብርሃን ሆነ ሌሊቱ ነጋ
አዋጅ ተሰማኝ ከአሪያም የወጣ
ጌታ አላለፈኝ ገባ ከቤቴ
ልዘምርለት ሞልቷል ስለቴ
ስራዬን ሰርቶልኝ ኧረ እንዴት አልዘምር
ሁሉን ለአደረገው ይሁንለት ክብር
ጠላቴን ጥሎልኝ ኧረ እንዴት አልዘምር
ሁሉን ለአደረገው ይሁንለት ክብር
አዝማች · Chorus
ይሁንለት ክብር (፰x)
እግዚአብሔር ብቻ መልካም ነው እግዚአብሔር ብቻ መልካም
በክፉ ቀን መሸሸጊያ እንደእርሱ ያለ የለም (፪x)
እንደእርሱ ያለ የለም (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አይልኝ አይልኝ ጌታ ከላይ ፈረደልኝ
የጠላቴን ዛቻ ከንቱ አደረገልኝ (፪x)
ፎክሮስ ነበር ጠላት በእኔ ላይ
ጌታ ገልብጦት ቆምኩኝ እራሱ ላይ
ድል አስለመደኝ ድል አየሁ በዐይኔ
አከብረዋለሁ እርሱ ነው ክብሬ
አዝማች · Chorus
እርሱ ነው ክብሬ (፰x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዘመን መጣልኝ የመገለጫ
ከአለት ንቃቃት በክብር መውጫ
የይልፈን ቃል ሰጠኝ ጌታዬ
ልውጣ ልገለጥ በምሥጋናዬ
ስራዬን/ጠላቴን ሰርቶልኝ ኧረ እንዴት አልዘምር
ሁሉን ላደረገው ይሁንለት ክብር (፪x)
አዝማች · Chorus
ይሁንለት ክብር (ይሁንለት) (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ